ዋና ስራ አስፈጻሚው የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ የስራ እንቅስቃሴን ጎበኙ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍስሃ ይታገሱ የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን የስራ እንቅስቃሴን ተመልክተዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚው በኢንዱስትሪ ፓርኩ እየተሰሩ ያሉ የኢንቨስትመንት ስራዎችን እንዲሁም የአምራች ኩባንያዎችን የስራ እንቅስቃሴ ፤ በአንድ ማዕከል ለኢንቨስተሮች እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶችን ከመመልከታቸው በተጨማሪ ከፓርኩ ማኔጅመንት አባላት ጋር በመሆን የፓርኩን የ11 ወራት እቅድ አፈፃፀም ገምግመዋል ፡፡
ዶ/ር ፍስሃ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኙ ኩባንያዎችን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በፓርኩ ኢንቨስት ካደረጉ ባለሀብቶች ጋርም ውይይቶችን አድርገዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈፃሚው የፓርኩን እቅድ አፈጸጸም ከመገምገማቸው በተጨማሪ በአዲሱ በጀት ዓመት በመጀመሪያ ምዕራፍ በመቶ ቀናት መከናወን በሚገባቸው ዋና ዋና ተግባራት ላይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡
IPDC CEO visited Bole Limi Industrial Park
Industrial Parks Development Corporation CEO, Dr. Fisseha Yitagesu, observed the current activity of Bole Limi Industrial Park.
The CEO oversees the investment activities being carried out in the industrial park as well as the activities of manufacturing companies. In addition he saw the services being provided to investors in one stop service, also reviewed the performance of the park's 11-month plan together with the park management.
Dr. Fisseha toured the companies in Bole Lemi Industrial Park and held discussions with investors who have invested in the park.
In addition to evaluating the current performance of the park's plan, the CEO set directions on the main activities that should be carried out in the first phase of the new fiscal year.