• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 5 months ago
  • 468 Views

አረንጓዴ አሻራ

የኮርፖሬሽኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በድሬዳዋ የነፃ ንግድ ቀጠና በይፋ ተጀመረ 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና በይፋ ተጀምሯል። 

የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብሩን የ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱ እና የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሀር በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ቅጥር ግቢ በይፋ አስጀምረዋል። 

በመርሀ ግብሩ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱንና  ከንቲባ ከድር ጁሀርን ጨምሮ የካቢኔ አባላት ፤ የኮርፖሬሽኑ አመራሮች ፤ የከተማዉ ወጣቶች እና ሴቶች ፤ የፀጥታ አካላት ፤ የነፃ ንግድ ቀጠናው ማህበረሰብ እንዲሁም ሌሎች አካላት ተሳታፊ ሆነዋል ። 

በነፃ ንግድ ቀጠናው በዛሬው እለት በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የተተከሉ ችግኞች ለምግብነት የሚውሉ ሲሆኑ  የማንጎ ፤ የዘይቱን ፤ የፓፓያ እና የብርትኳን ችግኞች ይገኙበታል። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በመላው ሀገሪቱ በሚያስተዳድራቸው ግዙፍ የኢንቨስትመንት ማዕከላት በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ሀገር በቀል ችግኞች የሚተከሉ ይሆናል። 

ባለፉት አመታት በኢንዱስትሪ ፓርኮች በተለያዩ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብሮች የተተከሉ ችግኞች ለምግብነትና ለጥላነት የሚውሉ ሲሆን የመፅደቅ ምጣኔያቸውም ከ85.በመቶ በላይ መሆኑ ተመላክቷል። 

IPDC 2016's Green Legacy Program has officially launched 

This year's Green Legacy Program of Industrial Parks Development Corporation has been officially launched at Dire Dawa Free Trade Zone. 

The Green Legacy program was officially launched by Industrial Parks Development Corporation CEO Dr. Fisseha Yitagesu, and the Mayor of Dire Dawa City, Kedir Juhar, at the premises of the Dire Dawa Free Trade Zone. 

Industrial Parks Development Corporation CEO, Dr. Fisseha Yitagesu, Mayor of Dire Dawa City, Keder Juhar, Cabinet members, Youth and womens of the city, security agencies, and other bodies from The free trade zone community were participated in the program. 

The seeds planted in the free trade zone today under the Green Legacy  program are edible and they include Mangos, papaya and orange seedlings. 

In this year's Green Legacy program, more than 1.2 million indigenous seeds will be planted in the huge investment centers managed by the Industrial Parks Development Corporation across the country. 

So far, seeds planted in various Green Legacy programs in industrial parks are edible and their developing rate is more than 85.1%.

#GreenLegacy