የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው ግዙፍ የኢንቨስትመንት ማዕከላት አንዱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና ነው።
የቀጠናው የእሳትና ድንገተኛ ብርጌድም በዛሬው እለት ጠዋት በድሬዳዋ ከተማ አሸዋ በመባል በሚጠራው የገበያ ስፍራ የተነሳውን የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ለማዋል በተሰራው ስራ የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል፡፡
የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣና የእሳትና ድንገተኛ ብርጌድ አባላት በከተማዋ በአሸዋ የገበያ ስፍራ የተነሳውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ባደረገው የተለመደ ርብርብ የበኩሉን ማህበራዊ ኃላፊነት ተወጥቷል፡፡
የነጻ የንግድ ቀጠናው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አህመድ ሰይድ እንደገለጹት ከጧቱ 2 ሰዓት የተነሳውን እሳት አደጋ ተከትሎ ከከተማ አስተዳደሩ በተደረገለት ጥሪ ወደ ቦታው የእሳት አደጋ ብርጌዱን በመላክ ማሰማራቱንና እሳቱም በቁጥጥር ስር እንዲውል የበኩሉን አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡
በዚህም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ነፃ ንግድ ቀጠናው ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በመላ ሀገሪቱ ገንብቶ በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነጻ የንግድ ቀጣና ባቋቋማቸው ዘመናዊና ፈጣን የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ብርጌዶች የፓርኮቹን ደህንነት ከማስጠበቁ በተጨማሪ በከተሞቹ አካባቢ የእሳት አደጋዎች ሲከሰቱ በመከላከል ረገድ ሃገራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡