ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል - አንባቢ ትውልድም ሀገር ይገነባል! ፤ ክረምትም ለንባብ ይመቻል !!
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አንባቢነት እንዲዳብርና ባህል ሆኖ እንዲቀጥል ለማስቻል ለአመራሮችና ፈፃሚዎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ መፅሀፍቶችን ማበርከት ጀምሯል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰም በውጪ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ፤ በዋልታ ሚዲያ እና በአብርሆት ቤተ መፃህፍት በጋራ "የሁለት ውሀዎች ዐቢይ ስትራቴጂ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን መፅሀፍ ለአመራሮችና ለፈፃሚዎች አበርክተዋል።
ይህ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በተለይም የእረፍት ጊዜን በማንበብ የማሳለፍ ልምድ በኮርፖሬሽኑ አመራርና ሰራተኞች ዘንድ እንዲዳብር ለማድረግ ይሰራል።
መልካም ንባብ!