• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 4 months, 1 week ago
  • 239 Views

በ1.2 ቢሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባ ኩባንያ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

በ1.2 ቢሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባ ኩባንያ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ 1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ፈሰስ ተደርጎበት ለሚገነባ ኩባንያ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡

የመሰረት ድንጋዩን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም ፤ የኮርፖሬት ሀብት አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አለማየሁ ሰይፉ እና የፔሪ ሜትር ኮንሰልቲንግ ማኔጅንግ ዳይሬክተር ቤተልሄም ጥላሁን ጋር በጋራ አስቀምጠዋል።

ፔሪ ሜትር ኮንሰልቲንግ እና ትሬዲንግ የተሰኘው ኩባንያ ከጤፍ የተለያዩ ስናኮችንና ደረቅ የምግብ ዓይነቶችን ለማምረት ለሚገነባው ማምረቻ ነው የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠው።

የኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም የመሰረት ድንጋዩ በተቀመጠበት ወቅት እንደተናገሩት ባለፉት 3 ዓመታት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለመጨመርና የባለሀብቶችን ቁጥር ለማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ ሪፎርሞች መተግበራቸውንና በዚህም ተጨባጭ ለውጥ የመምጣቱ ማሳያ ይህ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት ኩባንያ ነው ብለዋል።

አቶ ካሚል ኮርፖሬሽኑ ይህን አጠናክሮ ለማስቀጠል ወደ ኮርፖሬሽኑ ለሚመጡ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ማምረቻውን በ11 ሄክታር የለማ መሬት ላይ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የፔሪ ሜትር ኮንሰልቲንግ ኩባንያ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚደረግበት ሲሆን የግንባታ ስራው ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር ምርቶቹን ወደ አውሮፓ ፤ አሜሪካ እና የሩቅ ምስራቅ ሃገራት ኤክስፖርት እንደሚያደርግ ተገልጿል ።

Corner stone was laid to build a company with an investment capital of 1.2 billion birr

The corner stone was laid for a company that will be built at Bole Lemi Industrial Park with an investment capital of more than 1.2 billion birr.

Perimeter Consulting and Trading PLC laid the corner stone for a factory to produce various types of snacks and foods from teff.

Industrial Parks Development Corporation Operation Division deputy CEO Kamil Ibrahim, Corporate Resource Management Deputy CEO Alemayheu Seifu and Perimeter Consulting and trading PLC Managing Director Betelhem Tilahun laid the corner stone together.

Kamil Ibrahim, IPDC Deputy CEO, stated that, in the past 3 years, various reforms have been implemented by IPDC to increase the flow of investment in industrial parks and to increase the number of investors, and he said that the corner stone that is laid in Bole lemi industrial park is the best example.

Perimeter Consulting and trading PLC, which laid the corner stone to build its manufacturing facility on 11 hectares of service land in Bole Lemi Industrial Park, will invest more than 1.2 billion birr and export the products to America and Far East countries.

#Invest_In_Zero_Waiting_Time_Bureaucracy