ኮርፖሬሽኑ ኢትዮጵያን የኤሮስፔስ ኢንደስትሪ ማዕከል የሚያደርግ የውል ስምምነት ተፈራረመ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ኢትዮጵያን ከአፍሪካ በቀዳሚነት የኤሮስፔስ ኢንደስትሪ ማአከል የሚያደርግ የውል ስምምነት ናሽናል ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከተሰኘ ሃገር በቀል ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል፡፡
የውል ስምምነቱን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አክሊሉ ታደሰና የናሽናል ኢንቨትመንት ግሩፕ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ካፕቴን አበራ ለሚ ተፈራርመዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ በስምምነት ስነ ስርዓቱ ወቅት እንደገለጹት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የሃገር ውስጥ ባለሃብቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ በሃገር አቀፍ ደረጃ የተተገበሩ የሪፎርም ስራዎችን መሰረት በማድረግ በኮርፖሬሽኑ በርካታ የሪፎርም ስራዎች መሰራታቸውንና ለዚህም በዛሬው እለት የስምምነት ፊርማ የተፈራረመው ኩባንያ ትልቅ ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አቶ አክሊሉ በተጨማሪም በኮርፖሬሽኑ በኩል በሁሉም ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነጻ የንግድ ቀጣና አቅም ያላቸውንና ተወዳዳሪ የሆኑ ሀገር በቀል ባለሃብቶችን ለመሳብ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ከኮርፖሬሽኑ ጋር አብረው ለመስራት የሚመጡ ባለሃብቶችን ተቀብሎ ለማስተናገድና ያለምንም ውጣ ውረድ ስራ እንዲጀምሩ ለማድረግ ፈጣንና ዘመናዊ የአሰራር ስረዓትን (Zero waiting time) መዘርጋታቸውን አሳውቀዋል።
የናሽናል ኢንቨስትመንት ግሩፕ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ካፕቴን አበራ ለሚ በበኩላቸው ኩባንያው ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የአውሮፕላን ክፍሎችን በማምረትና በመገጣጠም ወደ ተለያዩ የአለም ሃገራት እንደሚያቀርብ ገልጸዋል፡፡
ኩባንያው ስራ ሲጀምር ከቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ አቅራቢያ የሚገኘውን የቂሊንጦ ሳይንስ አና ተክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲን ፤ የኤሮስፔስና ኤሮኖቲክስ የምርምር ማእከል ለማድረግ እና ተማሪዎቹን አና መምህራኑንም በስራው ለማሳተፍ እቅድ እንዳለው ካፕቴን አበራ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ኩባንያው በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ110 ሚሊዮን ዶላር በላይ ፈሰስ በማድረግ 14 ሄክታር የለማ መሬት ከኮርፖሬሽኑ የሚረከብ ሲሆን ለስራው የሚያስፈልጉትን ህንጻዎች ገንብቶና ማሽነሪዎችን ተክሎ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ ከ1,000 በላይ ለሚሆኑና በዘርፉ ለሰለጠኑ ባለሙያዎች የስራ እድልን ይፈጥራል፡፡
IPDC Signed an Agreement to Make Ethiopia the Hub of Aerospace Industrial Production
Industrial Parks Development Corporation (IPDC) signed an agreement with the locally established National Investment Group (NIG) to create the premier aerospace manufacturing hub in Africa.
The agreement was signed by Mr. Aklilu Tadesse, CEO of IPDC and Captain Abera Lemi, Managing Director of National Investment Group.
Mr. Aklilu stated at the signing ceremony that IPDC is working to increase the participation of local investors in industrial parks. As his statement the corporation has undertaken several reforms and today’s agreement with National Investment Group, is a clear example of the outcome of the reforms.
Mr. Aklilu added that IPDC is working to attract capable and competitive local investors into industrial parks and free trade zones by streamlining the processes, and is ready more than ever, to make sure that investors can implement their projects as quickly and efficiently as possible.
Founder of the National Investment Group, Captain Abera Lemi, on his part stressed that his company would work with various aircraft and parts manufacturers to produce and assemble aircraft components in Ethiopia and supply to the global market.
National investment Group will receive 14 hectares of service land from IPDC and the group plans to construct buildings, import and install the machineries on the site as soon as possible.
At full capacity, the group plans to create jobs for over 1,000 citizens and Additionally, to work with Kilinto Science and Technology University to create a world-class aerospace and aeronautics research institution and to make students and professors of the university fully participate in the process.