• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 5 months, 1 week ago
  • 408 Views

የፓኪስታን ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ

የፓኪስታን ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በኢንቨስትመንት የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ የመሰማራት ፍላጎት ያለው የፓኪስታን ኩባንያ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ማክተር ከተሰኘው የፓኪስታን ኩባንያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሻህናዋዝ ሳጂድ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው በውይይታቸውም መንግስት ለፋርማሲዩቲካል ዘርፍ የሰጠውን ትልቅ ትኩረት ፤ ኮርፖሬሽኑም ለዘርፉ ያቀረባቸውን ዘርፈ ብዙ ማበረታቻዎችንና የተሟላ መሰረተ ልማት እንዲሁም ዘመናዊና ባጠረ ቢሮክራሲ የሚሰጠውን ( Zero Waiting bureaucracy ) ኢንቨስትመንት ተኮር አገልግሎት ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከውይይቱ ባሻገርም የኩባንያው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሻህናዋዝ ሳጂድ የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክን መሰረተ ልማትና ወቅታዊ የምርት እንቅስቃሴ ሂደት ጎብኝተዋል።

ማክተር ኢንተርናሽናል መቀመጫውን ፓኪስታን ያደረገ ከ40 ዓመታት በላይ ልምድ ያለው የፋርማሲዩቲካል ግዙፍ ኩባንያ ሲሆን ከአለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመስራት ምርቱን በኤዢያ ፤ በአፍሪካ ፤ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና በሌሎችም የአለም ሀገራት በማከፋፈል ላይ ይገኛል።

A Pakistani company expressed interest in investing in industrial parks

Pakistani company showed interest in engaging in the pharmaceutical sector in Kilinto Industrial Park.

Industrial Parks Development Corporation CEO Aklilu Tadesse held a discussion with Dr. Shahnawaz Sajid, President of the company.

In the discussion, IPDC CEO Aklilu Tadesse mentioned to the company president, the great attention given by the government to the pharmaceutical sector and gave a detailed explanation of the fiscal and non-fiscal incentives. He added pointed out ideas related to infrastructure provided by the corporation to the sector as well as the investment services provided with modern and shorter bureaucracy which is 'Zero Waiting bureaucracy'.

Apart from the discussion, the company's president, Dr. Shahnawaz Sajid, visited the infrastructure and current production activities of Kilinto Industrial Park.

Macter International limited is a giant pharmaceutical based in Pakistan with over 40 years of experience working with international partners and has a market for its products in Asia, Africa, United Arab Emirates and other countries of the world.

#Invest_In_Zero_Waiting_Time_Bureaucracy