• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 5 months, 1 week ago
  • 356 Views

የአዳማ ሁናን ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ

ላለፉት 5 ዓመታት ግንባታው የዘገየውን የአዳማ ሁናን ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታን ለማስጀመር የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከቻይና ሁናን ግዛት ቻንግሻ ከተማ ከመጡት ከፍተኛ የመንግስት ልዑካንና የልዑኩ መሪ ው ዣዎሹ ጋር የአዳማ ሁናን ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታን ለማስጀመር የሚያስችል የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

አቶ አክሊሉ በውይይቱ የአዳማ ሁናን ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታን ለማስጀመር ባለፈው 1 ዓመት ሰፊ ስራ መሰራቱን ገልፀው አሁን ላይ የወሰን ማስከበር፤ የይዞታ ማካለልን ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ የቅድመ ግንባታ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ለልዑኩ አስገንዝበዋል።

የሁናን ግዛት ከፍተኛ የስራ ኃላፊ የሆኑት ው ዣዎሹ በበኩላቸው የአዳማ ሁናን ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታን ለማስጀመር የሚያስችል ልዩ ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ስራ መግባታቸውን የገለፁ ሲሆን ስራውን በአጭር ጊዜ ለማስጀመር እንደሚሰሩ አሳውቀዋል፡፡

የአዳማ ሁናን ኢንዱስትሪ ፓርክ በ108 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ እና በቻይናውያን ባለሀብቶች ግንባታው የሚካሄድ ሲሆን ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅም በተለያዩ ዘርፎች ከ25ሺ በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ወጣቶችና ሴቶች የስራ እድልን የሚፈጥር ይሆናል፡፡

A discussion was held to start the construction of Adama Hunan Industrial Park

IPDC CEO, Aklilu Tadesse, held a bilateral meeting with Mr. Wu Zhaoshu, a senior government official from Changsha City, Hunan Province, China, and other senior officials to start the construction of Adama Hunan Industrial Park.

Mr. Aklilu stated that extensive work has been done in the last 1 year to start the construction of Adama Hunan Industrial Park, and now the enforcement of boundaries and other related pre construction works, including land demarcation, has been completed.

Mr. Wu Zhaoshu, the senior official of Hunan Province, said that he has established a special committee to start the construction of Adama Hunan Industrial Park and said that the project will start in a short period of time.

Adama Hunan Industrial Park will cover a total 108 hectares of land and will be built by Chinese investors. When the construction is done, it will create job opportunities for more than 25 thousand local youth and women citizens in various fields.

#Invest_In_Zero_Waiting_Time_Bureaucracy