• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 7 months, 2 weeks ago
  • 505 Views

የፋይናንስ ሚኒስትሩ መልዕክት

"ሚስጥራዊ የደህንነት ማረጋገጫ ያላቸው የህትመት ውጤቶች በሀገራችን መመረቱ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአህጉሪቱም የሚታየውን ክፍተት የሚሸፍን ነው" - አህመድ ሺዴ 

ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸውና ሚስጥራዊ የደህንነት ማረጋገጫ ያላቸው ሰነዶች ህትመት በኢትዮጵያ መመረት መጀመሩ እንደ ሀገር ብቻ ሳይሆን እንደ አህጉር በዘርፉ የሚታዩ ክፍተቶችን በእጅጉ የሚያስተካክል ነው ሲሉ የፋይናንስ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ገለፁ። 

ሚኒስትሩ ይህን የገለፁት በዛሬው እለት በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በዘርፉ በአፍሪካ የመጀመሪያዉ የሆነዉንና  ቶፓን ግራቪቲ ለሚገነባው የፓስፖርት፤  የብሄራዊ መታወቂያ ፤ የማስተር ካርዶችና ሌሎሌ መሰል የደህንነት ምርቶችን በማይክሮ ቺፕስ በመታገዝ የሚያመርት ኩባንያን  የመሰረት ድንጋይ በተቀመጠበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ነው። 

አቶ አህመድ በኢትዮጵያ እያደገ ለመጣው የህትመት ፤ የፓኬጂንግና የዲጂታል አሰራሮች ተግባራዊነት እድገት የኩባንያው መገንባት አስፈላጊነቱ የጎላ ሚና እንደሚኖረው አንስተዋል። 

ኢትዮጵያ በኢኮኖሚው ዘርፍ እያስመዘገበች ኒያለችው እድገት ለማፋጠንና ሀገራዊ ዲጂታላይዜሽንን በአጭር ጊዜ እውን ለማድረግና መሰል የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በተጨማሪ ለማስፋፋት የቶፓን ግራቪቲ ኩባንያ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ሚኒስትሩ ጨምረው ገልፀዋል። 

በዛሬው እለት በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ እንዲገነባ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት ቶፓን የተሰኘው ኩባንያ በዓመት 5.6 ሚሊዮን ፓስፖርቶችን እንዲሁም 28 ሚሊዮን የሚሆኑ የተለያዩ ዲጂታል ካርዶችን የማምረት አቅም አለው። 

'The production of printing products with important security certification in our country covers the gap seen not only in Ethiopia but also in the continent' - Ahmed Shide 

The production of printed materials of high importance and security certification in Ethiopia will fill the gaps seen not only as a country, but as a continent, said Finance Minister Ahmed Shide. 

The minister said this today at the Ground Breaking ceremony of a company named Topan Gravity that manufactures Passports, Master Cards, National ID and similar products with the help of microchips at Bole alemi Industrial Park. 

Mr. Ahmed pointed out that the company will play an important role in the development of the growing development of publication, packaging
and the application of digital processes in Ethiopia. 

The Minister added that Topan Gravity Company will make a great contribution to accelerate the progress that Ethiopia is achieving in the economic sector and to realize national digitalization. 

Topan Gravity Ethiopia Plc , which will be built in Bole Lemi Industrial Park has the capacity to produce 5.6 million passports and 28 million different digital cards per year.

#Invest_In_Zero_Waiting_Time_Bureaucracy