• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 5 months, 3 weeks ago
  • 404 Views

የ 55 ሚሊዮን ዶላሩ ግዙፍ ኢንቨስትመንት

በ55 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ለፓስፖርት ፤ ብሄራዊ መታወቂያና መሰል የደህንነት ምርቶችን ለማምረት የሚያስችል ኩባንያ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ 

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፓስፖርት ፤ ብሄራዊ መታወቂያ እና መሰል ምርትቶችን የሚያመርት  ቶፓን ግራቪቲ የተሰኘ ኩባንያ ለሚገነባው ማምረቻ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ። 

የመሰረት ድንጋዩን ፤ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ፤ የብሔራዊ ባንክ ገዢዉ ማሞ ምህረቱ ፤ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ አብዱራህማን ኢድ ፤ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ፤ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ፤ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮሪ ከቶፓን ግራቪቲ ኩባንያ አመራሮች ጋር በጋራ አስቀምጠዋል። 

በዛሬው እለት በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የቶፓን ግራቪቲ ኩባንያ ከ55 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የሚደረግበት ሲሆን ፓስፖርት ፤ ብሄራዊ መታወቂያ ፤ ኤቲኤም ካርድ ፤ ማስተር ካርዶችንና ሌሎችም ከፍተኛ ደህንነትና ቴክኖሎጂና ማይክሮ ቺፕሶችን የሚጠይቁ ህትመቶችን ጨምሮ የሚያመርት መሆኑ ታውቋል። 

ኩባንያው በጃፓን እና በኢትዮጵያውያን በጋራ ቅንጅት ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ለፓስፖርት እና ሌሎችም ህትመቶች ግዢ የሚወጣን ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሬ በማስቀረት፤ ለወጣቶችና ለሴቶች ከፍተኛ የስራ እድል በመፍጠር ፤ የቴክኖሎጂ ሽግግርን እውን በማድረግ  እየታየ ያለውን የፓስፖርት እጥረትና ችግር የሚቀርፍ እንዲሁም ለዲጂታል ኢትዮጵያ እውን መሆን የማይተካ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑ ተገልጿል። 

Corner stone was laid to build a company that produces passport, national ID and similar security printing with an investment cost of 55 million USD. 

Corner stone was laid at Bole Lemi Industrial Park for a manufacturing facility to be built with 55 million USD by Toppan Gravity, a company that manufactures passports, national ID and other security printing products. 

Minister of finance Ahmed Shide, Governor of the National Bank of Ethiopia Mamo Mehretu, Minister of Education Prof. Birhanu Nega, Ethiopian Investment Holding CEO Abdurahman Eid, IPDC CEO Aklilu Tadesse, Immigration and Citizenship Service Director Selamawit  Dawit, Japanese Ambassador to Ethiopia Shibata Hironori and other officials laid the corner stone today.

Toppan Gravity, whose corner stone was laid in Bole Limi Industrial Park today, has more than 55 million USD  investment capital, and will produce Passport, National ID, ATM cards, Master Cards with micro chips and other security printings.

The manufacturing company will jointly be implemented by Japan and Ethiopians, and the implementation will be done in three phases. It has been stated that it will create job opportunities for citizens, solve the problem and lack of passports that has been seen in recent times and will contribute to the realization of digital Ethiopia.

#Invest_In_Zero_Waiting_Time_Bureaucracy