• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 8 months, 3 weeks ago
  • 681 Views

የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ክሊኒክ

የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ክሊኒክ 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገንብቶ በሚያስተዳድራቸው አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የኢንቨስትመንት ማዕከሎች ውስጥ ለኢንቨስተሮች እንዲሁም ለሰራተኞች የሚሆኑ አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችንና የተለያዩ አገልግሎቶችን በኢንቨስትመንት ማዕከሎቹ ያቀርባል። 

ኮርፖሬሽኑ ለኢንቨስተሮቹ እንዲሁም ብዛት ላላቸው ሰራተኞች ለኩባንያ እንዲሁም ለፓርክ ሰራተኞች ከሚያቀርባቸው አገልግሎቶች መካከል የተሟላ የጤና ጥበቃ አገልግሎት አንዱ ሲሆን ይህንንም አገልግሎት በሁሉም ኢንቨስትመንት ማዕከሎች ውስጥ በሚገኙት የጤና ጣቢያዎች እየሰጠ ይገኛል። 

ለዚህ ጥሩ ማሳያ ኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው የጤና ክሊኒክ ዋነኛው ሲሆን ክሊኒኩ የትኛውም ቦታ የሚገኝ መካከለኛ ክሊኒክ የሚሰጠውን የህክምና አገልግሎት መስጠት እንዲችል ተደርጎ የተዘጋጀ ነው። ለዚህም ከአ/ብ/ክ/መ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ህጋዊ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እና እውቅና በመድሀኒት አስ/ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 105/2004 አንቀፅ 16(5) መሰረት ተሰጥቶታል። 

በክሊኒኩ የኢንቨስትመንት ማህበረሰቡን ጤና ለመጠበቅ ለህሙማን የሚሆኑ የተለያዩ ለቅድመ ምርመራ የሚረዱ ሳይንሳዊ መለኪያዎች፤ መድሀኒቶች፤ አልጋዎች እንዲሁም መሰል ለመካከለኛ ክሊኒክ የሚያገለግሉ የህክምና ቁሳቁሶች በሙሉ ይገኛሉ።

Kombolcha Industrial Park Clinic

Industrial Parks Development Corporation provides essential infrastructure and services to investors and workers in the world-class investment centers it builds and manages around the nation.

Health care facilities is one of the services that IPDC provides to its investors and employees, and it is providing this service at the health care centers located in all investment centers around the nation.

A very good example of this is the health clinic at Kombolcha Industrial Park, which can provide the same medical services as any mid-level clinic.

The park received a legal qualification certificate and recognition from the Kombolcha City Administration Health Department bureau in accordance with Article 16(5) of Drug Control Decree No. 105/2004.

In order to protect the health of the investment community in the clinic, pre checkup scientific materials, medicines, beds for patients and similar medical equipments for intermediate response are available in the park.