በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው ትራይባስ ኩባንያ ምርቶቹን ለአሜሪካን ገበያ እያቀረበ ነው
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው ግዙፍ የኢንቨስትመንት ማዕከሎች አንዱ በሆነው ኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚገኘው ትራይባስ የጨርቃጨርቅና አልባሳት አምራች ኩባንያ ምርቶቹን ለአሜሪካን ገበያ እያቀረበ ይገኛል ።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከስራ አመራር አባላቶቻቸው ጋር የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።
በምልከታቸውም በፓርኩ የጨርቃ ጨርቅ አልባሳት እያመረተ የሚገኘውን ትራይባስ ኩባንያ የምርት እንቅስቃሴ የጎበኙ ሲሆን የኩባንያውም አሁናዊ የስራ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን ገልፀዋል።
ኩባንያው አሁን ላይ ዘመናዊ ሙሉ አልባሳቶችን እያመረተ የሚገኝ ሲሆን ምርቶቹንም በዋናነት ለአሜሪካ ገበያ እያቀረበ ይገኛል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በምልከታቸው ወቅት ፓርኩ ያለበት የስራ እንቅስቃሴና አለምአቀፋዊ ገበያ ተደራሽነት አበረታች መሆኑን አንስተው ፤ አሁን ላይ በፓርኩ ካሉ የማምረቻ ሼዶች 90 በመቶ ያህሉ በዉጪና በአገር ዉስጥ ባለ ሀብቶች መያዙን ገልፀዉ ኮርፖሬሽኑ ተጨማሪ ኢንቨስትመንቶች ወደ ፓርኩ እንዲገቡ እንዱሁም በምርት ሂደት ላይ የሚገኙት ትራይባስን የመሰሉ ኩባንያዎች ምርታቸውን በእጥፍ በማሳደግና ተጨማሪ አለም ዓቀፍ የገበያ አማራጮችን መጠቀም እንዲችሉ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
Tribus, a company located in Kombolcha Industrial Park, is exporting its products to the American market
Tribus, a textile manufacturing company located in Kombolcha Industrial Park, which is one of the huge investment centers managed by Industrial Parks Development Corporation, has revealed that it is supplying its products to the American market.
Industrial Parks Development Corporation CEO Aklilu Tadesse together with his management members observed the current activity of Kombolcha Industrial Park.
During their stay in kombolcha, they visited the production activity of a foreign company called Tribus, which is producing textile clothes in the park, and they also stated that the production activity of the company is encouraging.
The company currently manufactures full suits and casual coats and supplies its products mainly to the US market.
IPDC CEO Aklilu Tadesse, during his observation, pointed out that the activity of the park and the accessibility of the international market are encouraging. He stated that 90% of the production sheds in the park are occupied by foreign and domestic manufacturers and pointed out that IPDC is working to bring more investments into the park and that companies such as Tribus, which are in operation, are working to double their production and use more international market options.
#invest_in_zero_waiting_time_bureaucracy