• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 7 months, 3 weeks ago
  • 536 Views

የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክት

"ፕሮጀክቱ የሐዋሳ ኢንዱስትሪየሐዋሳን የኢንቨስትመንት ፍሰት የሚጨምር ነው" - ሀብታሙ ሐይለሚካኤል 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከጀርመን የስራ እድል ፈጠራ ማስተባበሪያ ቢሮ አይ ኤፍ ኢ ( IFE ) ጋር የተፈራረመው የ1.2 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን የኢንቨስትመንት ፍሰት በእጅጉ ይጨምራል ሲሉ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ሐይለሚካኤል ገልፀዋል። 

ዳይሬክተሩ ይህን የገለፁት ኮርፖሬሽኑ የስምምነት የፊርማ ስነ ስርዓቱን ከጀርመኑ ማስተባበሪያ ድርጅት ጋር ባከናወነበትት ወቅት ነው። 

አቶ ሀብታሙ ጨምረውም የተደረገው ስምምነት በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ አሁን ያለውንና ከ24 ሺ በላይ የደረሰውን የስራ እድል ፈጠራ ለማሳደግ ብሎም ፓርኩ በሙሉ አቅሙ መንቀሳቀስ እንዲችልና በፓርኩ ያለውን የስራ እድል ፈጠራ 60 ሺ ለማድረስ የተያዘውን ግብ በእጅጉ ለማሳካት የሚረዳ መሆኑን አንስተዋል። 

ኮርፖሬሽኑ አማራጭ የፋይናንስ ምንጮችን አሟጥጦ ለመጠቀም እያደረገ ያለውን ተግባር አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ያሉት  አቶ ሀብታሙ ሀገሪቱ የያዘቻቸውን የኢንዱስትሪ ግብ ለማሳካት  ከሚያግዙ ሀገራት እና የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ጋር የሚደረጉ መሰል ጠንካራ ግንኙነቶች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አፅኖት ሰጥተዋል ።

"The project will increase the flow of investment of Hawassa Industrial Park" - Habtamu Hailemichel 

The 1.2 million euro Grant Agreement signed by Industrial Parks Development Corporation and The Facility Investing for Employment (IFE) will greatly increase the investment flow of Hawasa Industrial Park, said Habtamu Hailemichael, Director General of Public Enterprises Holding and Administration. 

The director stated this on the agreement signing ceremony of IPDC and IFE. 

Mr. Habtamu also mentioned that the agreement made in Hawasa Industrial Park will help to increase the current job creation which has reached more than 24 thousand. He additionally mentioned that the project will support the park to be able to operate at its full capacity and it will greatly help to achieve the goal of creating 60 thousand jobs in the park. 

Mr. Habtamu thanked the German government for its support and reminded that strong cooperation with countries and international institutions that help the country's vision of rapid development should continue to be strengthened.