• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 8 months, 1 week ago
  • 532 Views

የዋና ስራ አስፈፃሚው መልዕክት

"አላማችንን ደግፈው በትብብር ከሚሰሩ አጋር ተቋማት ጋር ያለንን ግንኙነት አጠናክረን እንቀጥላለን" - አክሊሉ ታደሰ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በጋራ አላማ በትብብር ከሚሰሩ አጋር ተቋማት ጋር የሚደረገው ተቋማዊ ግንኙነት ይበልጡን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፁ።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን የገለፁት ኮርፖሬሽኑ ከጀርመን የስራ እድል ፈጠራ ማስተባበሪያ ቢሮ  አይ ኤፍ ኢ  ጋር የ1.2 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት በተፈራረመበት ወቅት ነው።

ዋና ስራ አስፈፃሚው የፋይናንስ ድጋፉን ያደረገውን ተቋም አመስግነው  በቀጣይም የኮርፖሬሽኑን አላማ ግብና ራዕይ ከሚደግፉ አጋር ተቋማት ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶች እንደሚጠናከሩ አረጋግጠዋል። አክለውም ከስራ እድል ፈጠራ ፤ ከኢንቨስትመንትና ከኢንቨስተሮች ፍላጎት ከማሳደግ ጋር ተያያዥ የሆኑ  መሰል ፕሮጀክቶች የሚኖራቸው ሚና የማይተካ መሆኑን ተናግረዋል ።

በተጨማሪም መሰል ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላቸው ፕሮጀክቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ የአለም አቀፍ ተቋማት እውቀትና ልምድ እንዲሁም ድጋፍና ክትትል ትልቅ ትርጉም እንዳለው ጠቅሰዋል።

ስምምነቱ ተግባራዊ የሚደረግባቸው ፕሮጀክቶች እንዲሳኩና የታለመላቸውን ግብ እንዲመቱ በጋራ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባም አቶ አክሊሉ አሳስበዋል።

"We will continue to strengthen our relationship with Stakeholders who support and share our vision" - Aklilu Tadesse

Aklilu Tadesse, Industrial Parks Development Corporation CEO, stated that the corporation will continue to strengthened the relationship with partner stakeholders that work in cooperation with a common goal.

The CEO made this statement when the corporation signed a 1.2 million euro Grant agreement with The Facility Investing for Employment (IFE).

In his remark The CEO thanked the office for the financial support and pointed out that relations with partner stakeholders that support the goals and vision of the corporation will be strengthened. He additionally reminded that the value of such projects related to job creation and investment and investors' needs is irreplaceable.

Mr. Aklilu added that the knowledge and experience of international institutions, as well as the support and guidance, are greatly  important for the implementation of such multi-purpose projects.

Mr. Aklilu also underlined that the implementation of the project under the agreement should be done together with high determination to achieve the common goals.