• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 7 months, 3 weeks ago
  • 517 Views

የ1.2 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት

ኮርፖሬሽኑ ከጀርመን ኩባንያ ጋር የ1.2 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የጀርመን ድርጅት አስተባባሪ ከሆነው The Facility Investing for Employment ( IFE ) ጋር የ1.2 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራርሟል። 

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የጀርመኑ ማስተባበሪያ ቢሮ ኮርፖሬሽኑ የያዘውንና ግዙፍ ሀገራዊ አላማ የሆኑትን የስራ እድል ፈጠራን መጨመር፤ የውሀ አቅርቦት ተደራሽነትን ለማሳደግ እንዲሁም የአምራች ኩባንያዎች አቅም ማሳደግና እርካታን ለመጨመር በመተባበር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ የሚደነቅ ነው ብለዋል። ኮርፖሬሽኑም ፕሮጀክቱ በተያዘለት ግዜ ተጠናቆ በሙሉ አቅም ተግባራዊ እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደሚንቀሳቀስ አረጋግጠዋል። 

ኮርፖሬሽኑ በዛሬው እለት ከጀርመን የስራ እድል ፈጠራ ማስተባበሪያ ቢሮ "The Facility Investing for Employment" ( IFE ) ጋር የተፈራረመው ስምምነት በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የንፁህ ውሀ አቅርቦትን ለማሳደግ፤ የአምራች ኩባንያዎችን እርካታ በመጨመር ፓርኩ በሙሉ አቅሙ እንዲንቀሳቀስ እና ከ300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ያለመ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ ነው።

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ሐይለሚካኤል፤ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እንዲሁም የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብና እድገት ሚኒስትር ማስተባበሪያ ዶ/ር ዶሚኒካ ፕሪይዚንግን ጨምሮ ሌሎች ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

IPDC signed a 1.2 million euro Grant agreement with IFE

Industrial Parks Development Corporation has signed a 1.2 million euro Grant agreement with The Facility Investing for Employment (IFE).

Speaking during the Grant agreement signing ceremony, Industrial Parks Development Corporation CEO Aklilu Tadesse,
said that the agreement will enable IPDC to increase job creation, which is a huge national goal and IFE is admirable to provide financial support in order to increase access to safe and potable water supply and increase the capacity and satisfaction of manufacturing companies in Hawassa Industrial Park.

And he also confirmed that IPDC will work with high commitment to make the project completed on schedule and fully operational.

Today, IPDC signed a Grant agreement with The Facility Investing for Employment" (IFE) aiming to increase the supply of safe and potable water at Hawasa Industrial Park, to increase the satisfaction of the manufacturing companies so that the park can operate at full capacity and create job opportunities for more than 300 citizens.

At the signing ceremony, PEHA Director Habtamu Hailemichael, IPDC CEO Aklilu Tadesse, German Federal Ministry of Economic Cooperation and Development (BMZ) Dr. Dominika Preising, and other officials were present.