• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 7 months, 1 week ago
  • 503 Views

ፋርማሲዩቲካል እና አግሮ ፕሮሰሲንግ ሴክተር

"በኢትዮጵያ የፋርማሲዩቲካልና አግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ አዋጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻዎች ናቸው" - በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር 

በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙት  የህንድ አምባሳደር እና የአፍሪካ ህብረት ተወካይ አኒል ኩማር ራኢ በኢትዮጵያ የፋርማሲዩቲካልና አግሮ ፕሮሰሲንግ  የኢንቨስትመንት ዘርፎች አዋጭ መዳረሻዎች መሆናቸውን ገለፁ። 

አምባሳደሩ ይህን የገለፁት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ጋር በኤምባሲያቸው 
ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው። 

በውይይቱም ቀድመው የነበሩ ጠንካራ የኢንቨስትመንት ፤ የሰው ሀይል አቅም ግንባታ እና ተያያዥ ግንኙነቶችን ማጠናከር እንዲሁም አዳዲስ ኢንቨስተሮችን መሳብና ኢንቨስትመንትን ተግባራዊ ማድረግ ላይ ሰፊ ዉይይት ተደርጓል ። 

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ቀደም ከህንድ ኤምባሲ ጋር የነበረው ጠንካራ ግንኙነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ተጨማሪ የህንድ ባለሀብቶች በተለይም በፋርማሲዩቲካልና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲገቡ ለማድረግ መሰራት እንዳለበት አንስተዋል። 

በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር እና የአፍሪካ ህብረት ተወካይ አኒል ኩማር ራኢ ኢትዮጵያ ያላት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወጣት ሀይል እና ለፋርማሲዩቲካል ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት ለኢንቨስትመንት ምቹ መሆኑንና በተለይም ፋርማሲዩቲካል እና አግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፎች የኢንቨስትመንት መዳረሻዎች መሆናቸውን አንስተው በቀጣይ በጋራ መስራት የሚቻልባቸው ጉዳዮችን ለይቶ መንቀሳቀስ እንደሚገባ አሳውቀዋል። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ፤ በፋርማሲዩቲካልና በሌሎችም በርካታ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩ ፤ ከፍተኛ የስራ ዕድል እና የእዉቀት ሽግግር መፍጠር የቻሉ 13 ያህል  ግዙፍ የህንድ ኩባንያዎች የሚገኙ ሲሆን ህንድ ከቻይና ቀጥሎ ከፍተኛ ባለሀብቶችን በኢንዱስትሪ ፓርኮች በማሰማራት በሁለተኛ ደረጃ  መቀመጧ ይታወቃል ። 

"Pharmaceutical and agro-processing sectors in Ethiopia are viable investment destinations" - Anil Kumar, Ambassador of India to Ethiopia 

Anil Kumar Rai, Ambassador of India and African Union representative in Ethiopia, stated that the pharmaceutical and agro-processing sectors are viable investment destinations in Ethiopia. 

The Ambassador stated this during a discussion with Industrial Parks Development Corporation CEO Aklilu Tadesse and his management members. 

There were exchanges of ideas in the meeting on strengthen the investment relationship, human resource capacity building and  related relationships as well as attracting and new investors to industrial parks. 

IPDC CEO Aklilu Tadesse, said that the corporation will continue to strengthen its strong relationship with Indian Embassy and will work to attract more Indian investors, especially in the pharmaceutical and agro-processing sectors. 

Anil Kumar Rai, the Ambassador of India and African Union representative in Ethiopia, confirmed that Ethiopia has a large number of young people and the attention given to the pharmaceutical sector is conducive for investment and the embassy will identify issues that can be worked together to strengthen the current cooperation in the future. 

There are more than 12 Indian companies engaged in various investment sectors in the industrial parks and Dire Dawa Free Trade Zone managed by IPDC. After China, India  ranked second in terms of deploying large investors in industrial parks.