ኮርፖሬሽኑ ለዲቦራ ፋውንዴሽን የገንዘብ ድጋፍ አበረከተ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለዲቦራ ፋውንዴሽን የ3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበርክቷል።
ድጋፉን ለፋውንዴሽኑ መስራችና ባለቤት አቶ አባ ዱላ ገመዳ ያበረከቱት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ናቸው።
ዋና ስራ አስፈፃሚው አክሊሉ ታደሰ ድጋፉን ባበረከቱበት ወቅት ኮርፖሬሽኑ የሀገሪቱን የኢንቨስትመንት ፍሰት ከማሳለጥ በተጨማሪ እንደ ዲቦራ ፋውንዴሽን አይነት ለሀገር ትልቅ አበርክቶ ላላቸው ፕሮጀክቶች ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ እንደሆነ ተናግረዋል ።
መሰል ድጋፎችን ኮርፖሬሽኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ዋና ስራ አስፈፃሚው አረጋግጠዋል።
የገንዘብ ድጋፉን የተረከቡት የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራችና ባለቤት አቶ አባ ዱላ ገመዳ ይህን መሰል በጎ ተግባር በመፈፀሙ ኮርፖሬሽኑ ምስጋና እንደሚገባው ጠቁመው ይህ ተግባር ለሌሎች ተቋማት፤ ባለሀብቶችና ለሚመለከታቸው አካላት አርአያ የሚሆን ነው በማለት ተናግረዋል።
ኮርፖሬሽኑ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገለት ዲቦራ ፋውንዴሽን በአእምሮ እድገት ውስንነት ላይ የሚሰራ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን አላማውም የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ሰዎች ለሀገራቸው የሚጠቅሙ እንዲሆኑና ማህበረሰቡም እንደ ችግር እንዳይመለከተው ማድረግ ነው።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ድጋፍ ለሚሹ አካላት የአልባሳትና የቁሳሱስ ፤ የትምህርት መሳሪያዎችና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ሲያበረክት የቆየ ሲሆን በቅርቡም በአዳማ ከተማ ትምህርት ቤት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጡ አይዘነጋም።
IPDC donates 3 million birr to the Deborah Foundation
Industrial Parks Development Corporation donates 3 million birr to Deborah Foundation.
IPDC CEO Aklilu Tadesse, presented the donation to the foundation founder Mr. Abba Dula Gemeda.
Aklilu Tadesse said the corporation is fulfilling its social responsibility by supporting projects such as Deborah Foundation beyond its mission which is accelerating the flow of investment to realize industrialization. He assured that IPDC will continue to strengthen the same CSR activities.
Abba Dula Gemeda, founder of Deborah Foundation, said the corporation deserves to be thanked for its contribution and it is exemplary corporation for other institutions,
Deborah Foundation, which IPDC supported it 3 million birr donation is non profitable charity foundation working in childs with special needs and aims to ensure childs with intellectual disabilities benefit their country and their community.
Industrial Parks Development Corporation has been donating educational equipment, clothes and other materials for those who need support to fulfill its Corporate social responsibility. IPDC also recently laid a corner stone to build school in Adama city.