• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 7 months, 4 weeks ago
  • 422 Views

የዴንማርክ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ

የዴንማርክ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የስራ እንቅስቃሴን ተመለከቱ 

የዴንማርክ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ላረስ ሎኬ ራስሙሰ የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴን ተመልክተዋል። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የፓርኩን ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ ለሚኒስትሩ አስጎብኝተዋል። 

በጉብኝቱ ወቅትም ዋና ስራ አስፈፃሚው ስለኮርፖሬሽኑ የስራ እንቅስቃሴ፤ ስለሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነፃ ንግድ ቀጠና እንዲሁም ኢንቨስትመንትን የተመለከተ ገለፃ አድርገዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት 4 ዓመታት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ማሻሻያዎችን ተግባራዊ ማድረጉን እና ይህም ሀገሪቷ ካላት ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ፤ እምቅ የተፈጥሮ ሀብትና ወጣት የሰው ሀይል አንፃር ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ አስተዋፅኦ ማድረጉን ገልፀዋል። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገኙ አምራቾች ውጤታማ መሆናቸውን ብሎም የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ እያደረጉ እንደሚገኙ ለዚህም ሚኒስትሩ የጎበኙት ሺንትስ ኩባንያ ዋነኛ ተጠቃሽ መሆኑን አስታውሰዋል። 

የዴንማርክ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ላረስ ሎኬ ራስሙስ በቦሌ ለሙ ኢንዱስትሪ ፓርክ በነበራቸው ቆይታ ሺንትስ የተሰኘውን የጋርመንትና ቴክስታይል ግዙፍ ኩባንያ ተዟዙረው ተመልክተዋል። ከኩባንያው የስራ ኃላፊዎች ጋርም ስለ ምርት ሂደቱ ውይይት አድርገዋል። 

The Minister of Foreign Affairs of Denmark saw the activity of Bole Lemi Industrial Park 

Denmark's Minister of Foreign Affairs, Lars Løkke Rasmussen, observed the general activity of the Bole Lemi Industrial Park. 

Aklilu Tadesse, Industrial Parks Development Corporation CEO, gave the minister a tour of the park's current activities. 

During the visit, the CEO mentioned about the activities of the corporation and made a statement about the 13 industrial parks and free trade zones that IPDC manages, as well as the positive investment atmosphere. 

He also added that the Ethiopian government has implemented indigenous economic reforms in the last 4 years and it is contributing to making the country's potential natural resources and young human resources effective for the sector in terms of its advantageous geographical location. 

Mr Aklilu added that the manufacturers located in the industrial parks are successful and are implementing expansion projects, for which Shints company that the minister visited was the main reference. 

Denmark's Minister of Foreign Affairs, Lars Løkke Rasmus, visited Shints, a giant garment and textile company, during his stay at Bole Lemi Industrial Park. He also discussed the production progress with the company officials.