• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 7 months, 4 weeks ago
  • 397 Views

ኮርፖሬሽኑ እና በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያደረጉት ኢንቨስትመንት ተኮር ውይይት

"በህንድ የሚገኙ እምቅ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለመጠቀም በትብብር መስራት ያስፈልጋል" - አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ 

በህንድ ሀገር የሚገኙ እምቅ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለመጠቀም ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መስራት ያስፈልጋል ሲሉ በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ገለፁ። 

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በዛሬው እለት በህንድ ከኢትዮጵያ አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ጋር በበይነ መረብ ኢንቨስትመንት ተኮር ውይይት አድርገዋል።
 
ውይይቱ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገኙ የህንድ ባለሀብቶችን ማበረታታት፤ አዳዲስ የህንድ ባለሀብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ማስቻል እንዲሁም በሌሎች ኢንቨስትመንት ተኮር ዘርፎች በጋራ መስራት ላይ ያተኮረ ነበር። 

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ኮርፖሬሽኑ የተለያዩ ኢንቨስትመንት ተኮር ሪፎርሞችን ተግባራዊ በማድረግ በተለይም ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ እየሰራ መሆኑን አንስተው አሁን ያለውን መነቃቃት አጠናክሮ ለማስቀጠል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርርብ መስራት እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተዋል። 

በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ ከኤምባሲው ለሚመጡ የኢንቨስትመንት ጉዳዮች የሚሰጠው ቀልጣፋ ምላሽና አገልግሎት በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ገልፀው ይህም ይበልጥ በቅንጅት አብሮ ለመስራት እንደሚያነሳሳ አክለዋል። 

በዛሬው እለት በኮርፖሬሽኑ እና በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መካከል በተደረገው የበይነ መረብ ውይይት ወቅታዊ መረጃዎችን በመለዋወጥ፤ በተለይም በአግሮ ፕሮሰሲንግ፤ በጋርመንትና ቴክስታይል እንዲሁም በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ግዙፍ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤክስፖ በጋራ ለማዘጋጀት ከስምምነት ተደርሷል። 

'Working together with positive cooperation is must to take advantage of the potential investment opportunities in India' - Ambassador, Demeke Atanafu.

Ethiopia's ambassador to India, Demeke Atanafu stated that Working together in positive cooperation with stakeholders is must to take advantage of the potential investment opportunities in India.

IPDC CEO, Aklilu Tadesse, held investment related discussion with the Ethiopian ambassador to India, Demeke Atnafu. 

The discussion aims encouraging Indian investors in industrial parks, attracting new Indian investors to invest as well as working together in other investment-related sectors. 

IPDC CEO, Aklilu Tadesse, pointed out that the corporation is working to attract foreign direct investments by implementing various investment-oriented reforms, and emphasized the need to work in cooperation to continue the current postive investment atmosphere. 

Demeke Atnafu, Ethiopia's ambassador to India on his part said that he was pleased with the efficient response and service provided by the corporation to the investment issues coming from the embassy, adding that this would motivate to work together in collaboration. 

in today's online discussion, an agreement has been reached to jointly exchange current updated data’s and information and to organize a huge investment promotion expo focused on Agro Processing, Garment and Textile and Pharmaceutical sectors.