የኮርፖሬሽኑ የ 'Act Excellence' ሁለተኛ ዙር ፕሮግራም ቀጥሏል
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን "Act Excellence" በሚል ስያሜ የጀመረው ግዙፍ የሪፎርም ፕሮግራም አካል የሆነውና በሁለተኛው ዙር ከኮርፖሬሽኑ ዋናው ቢሮ እና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች የተወጣጡ የስራ ኃላፊዎች የሚካፈሉበት ስልጠና በቻይና ሀገር ይካሄዳል።
በተቋሙ በተለያዩ የስራ ክፍሎች የሚሰሩ ኃላፊዎችን እና ሰራተኞችን አቅም በማጎልበት የተጣለበትን ሀገራዊ ሀላፊነት ፕሮፌሽናል በሆነ መንገድ ለመወጣት ያለመው የ "Act excellence" ፕሮግራም ሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች በቻይና በሚካሄደው ስልጠና ለመሳተፍ በኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
ተሳታፊዎቹ በስልጠናው ያገኟቸውን እውቀቶች ፤ ልምዶችና ተሞክሮዎች ወደ ስራ ሲመለሱ በኮርፖሬሽኑ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን አጠናክረው ለማስቀጠል እንደሚያግዛቸው ሲጠበቅ ከስልጠናው በተጨማሪ ከተለያዩ ሀገራት ለተወጣጡ የስልጠናው ተሳታፊዎች ኮርፖሬሽኑን እንዲሁም በስሩ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ማዕከሎችን የማስተዋወቅና ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ የሚያብራራ ውይይት በማድረግ የጋራ ሀሳቦችን እንደሚለዋወጡ ይጠበቃል።
ኮርፖሬሽኑን ወክለው የሚጓዙት ተሳታፊዎች በቻይና ከሚካሄደው የስልጠና መድረክ በተጨማሪ በተለያዩ የቻይና ግዛቶች ያሉ ግዙፍ የማኑፋክቸሪንግ ኩባንያዎችና ኢንዱስትሪዎችን የሚመለከቱ ሲሆን በቻይና ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋርም ኢንቨስትመንት ተኮር የሁለትዮሽ ያካሂዳሉ ተብሏል።
#Act_Excellence