• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 5 months ago
  • 160 Views

የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ማምረቻ ሼዶች ሙሉ በሙሉ በባለሀብቶች መያዛቸው

"የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሙሉ በሙሉ በባለሀብቶች ተይዟል" - አክሊሉ ታደሰ 

በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኙ 19 የማምረቻ ሼዶች ሙሉ በሙሉ በባለሀብቶች እና በአምራች ኩባንያዎች መያዛቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ገልፀዋል። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን የገለፁት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሀፊና አስተባባሪ ዶ/ር ራሚዝ አላክባሮቭ ጋር በመሆን አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክን በጎበኙበት ወቅት ነው። 

በዛሬው እለት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሀፊ ጋር በመሆን በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያሉ አምራች ኩባንያዎችን እንዲሁም የፓርኩን አጠቃላይ ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው በጉብኝቱ ወቅት በፓርኩ ያሉ 19 የማምረቻ ሼዶች ሙሉ በሙሉ በዉጪና በአገር በቀል ባለሀብቶችና ኩባንያዎች መያዛቸውን እንዲሁም ከ 7 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን አንስተዋል። አሁን ላይም በኢንቨስትመንት መሰማራት ለሚፈልጉ ሀገር በቀልና የውጪ ባለሀብቶች ፓርኩ 2 ሄክታር የሚጠጋ የለማ መሬት ዝግጁ ማድረጉን ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለዋል። 

ለዚህ ውጤት መሳካት ኮርፖሬሽኑ ባለፈው 1 ዓምት የአምራች ዘርፍ ብዝሀነት ላይ እንዲሁም ለአምራቾች ተጨማሪ የገበያ አማራጮችን ማግኘት ላይ ያከናወናቸው የሪፎርም ተግባራት ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው ተጠቁሟል።

ማምረቻ ሼዶቹ በሀገር በቀል ኩባንያዎች እንዲሁም ከኖርዌይ፤ ከቻይና፤ ከህንድ ከአሜሪካ እና ከተለያዩ ሀገራት በተወጣጡ አምራቾች መያዙን ጠቁመው ባለፉት 6 ወራትም በፓርኩ ከ20 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተኪ ምርት መመረት መቻሉን፤ ከ18 ሚሊዮን ዶላር በላይ ደግሞ የገበያ ትስስር መፈጠሩን አሳውቀዋል። 

ከዚህ ቀደም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሀፊና አስተባባሪ ዶ/ር ራሚዝ አላክባሮቭ የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን መጎብኘታቸው እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በቅንጅት ሊሰራቸው የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ከዋና ስራ አስፈፃሚው አክሊሉ ታደሰ ጋር መወያየታቸው አይዘነጋም። 

"Adama Industrial Park is  occupied by investors" -  Aklilu Tadesse 

Industrial Parks Development Corporation
CEO, Aklilu Tadesse, said that 19 manufacturing sheds in Adama Industrial Park have been fully occupied by investors and manufacturing companies. 

The CEO stated this when he visited Adama Industrial Park together with the United Nations Assistant Secretary-General and Coordinator, Dr. Ramiz Alakbarov. 

Today, IPDC CEO, Aklilu Tadesse, together with the Assistant Secretary General of the United Nations, toured the manufacturing companies in Adama Industrial Park and observed the park's current activities. 

During the visit, the CEO mentioned that 19 production sheds in the park have been fully occupied by foreign and local investors and companies, and that employment opportunities have been created for more than 7,000 citizens. He pointed out that the park has prepared nearly 2 hectares of service land for local and foreign investors who are interested to invest. 

It has been pointed out that the reform activities carried out by the corporation in the last 1 year on sector diversification and finding more market options for the producers have a big role in achieving these results.

The production sheds are occupied by local companies as well as foreign manufacturers  from Norway,that China,  India, America and various countries. It is also mentioned  in the last 6 months, more than 20 million dollars worth of production to substitute import has been produced in the park and more than 18 million dollars worth of market linkage have been successfully created. 

Earlier last week, The Assistant Secretary-General and Coordinator of the United Nations, Dr. Ramiz Alakbarov, visited Bole Limi Industrial Park and discussed with IPDC CEO, Aklilu Tadesse on the areas of cooperation with the United Nations.

#Invest_In_Zero_Waiting_Time_bureaucracy