• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 10 months, 1 week ago
  • 592 Views

የግሎባል ኢንዲያ ቢዝነስ ፎረም ከፍተኛ ኃላፊዎች

ኮርፖሬሽኑ የብሪክስ አባል ሃገራት ያላቸውን እምቅ የኢንቨስትመንት አቅም አሟጥጦ ለመጠቀም በትኩረት ይሰራል-አክሊሉ ታደሰ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነፃ የንግድ ቀጣና የብሪክስ አባል ሃገራት ያላቸውን አቅም አሟጥጦ ለመጠቀም በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ ከግሎባል ኢንዲያ ቢዝነስ ፎረም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና በአግሮ ፕሮሰሲንግና ፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው የባለሃብቶች የልዑካን ቡድንን  ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው በውይይቱ ኮርፖሬሽኑ አሁን ላይ ከህንድ ፤ከሩሲያ፤ከቻይናና ከብራዚል ባለሃብቶች፤ኤምባሲዎችና የኢንቨስትመንት ተቋማት ጋር አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በፓርኮቹ ለመሳብ በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልጸው በተለይም የብሪክስ አባል ሃገራት ያላቸውን እምቅ የኢንቨስትመንት አቅም አማጥጦ ለመጠቀም የሚያስችል  ስራዎች በመስራት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ 

የግሎባል ኢንዲያ ቢዝነስ ፎረም ፕሬዚዳንት ዶክተር ጅቴንድራ ጆሺ ከህንድ የመጣው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተለይም በፋርማሲዩቲካልና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ለመሰማራት የሚያስችል ቅድመ ኢንቨስትመንት መረጃ ማጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡ 

የልዑካን ቡድኑ አባላት በፋርማሲዩቲካል፤አግሮ ፕሮሰሲንግ፤በሎጅስቲክስ እና ቴክስታይል የኢንቨስትመንት ዘርፎች በመስራት ላይ የሚገኙ ሲሆን የቂሊንጦ እና ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን የስራ እንቅስቃሴንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነጻ የንግድ ቀጣና የህንዳውያን ባለሃብቶች ተሳትፎን በየጊዜው እያደገ የመጣ ሲሆን አሁን ላይ ከ12 በላይ ግዙፍ ኢንቨስትመንት ያላቸው ህንዳውያን ባለሃብቶች በፋርማሲዩቲካል፤በቴክስታይል እና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፎች ላይ በመሰማራት ከ20 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ  የስራ እድል ፈጥረው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

“IPDC will work diligently to utilize the investment potential of the BRICS member countries” Aklilu Tadesse

The Industrial Parks Development Corporation is working hard to utilize the potential of BRICS member countries in its 13 industrial parks and Dire Dawa free trade zone.

Aklilu Tadesse , IPDC CEO, welcomed a delegation from the Global India Business Forum, including investors exploring opportunities in agro-processing and pharmaceuticals.

Aklilu expressed that IPDC is collaborating with investors, embassies, and investment institutions from India, Russia, China, and Brazil to attract new investments to the industrial parks, leveraging on the investment potential of BRICS countries.

Dr. Jitendra Joshi, President of the Global India Business Forum, stated that the Indian delegation has compiled pre-investment information to explore specific investment opportunities within Ethiopia's industrial parks, particularly in the pharmaceutical and agro-processing sectors.

Members of the delegation, representing diverse sectors like pharmaceuticals, agro-processing, logistics, and textiles has already visited Kilinto and Bole Limi Industrial Parks to observe the ongoing operations.

Indian investors, with over 12 major investments in the industrial parks and Dire Dawa free trade zones managed by IPDC, have created permanent employment opportunities for more than 20,000 Ethiopian citizens in the pharmaceutical, textile, and agro-processing sectors.