• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 5 months, 2 weeks ago
  • 179 Views

የኮርፖሬሽኑ የ6 ወራት ገቢና ትርፋማነት

ኮርፖሬሽኑ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ከ992 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በ 2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈፃፀም ከ992 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ ተገልጿል። 

ይህ የተገለፀው ኮርፖሬሽኑ በድሬዳዋ እያደረገ ባለው የበጀት ዓመቱ የ6 ወራት የእቅድ ግምገማ  መድረክ ላይ ነው። 

ኮርፖሬሽኑ ይህንን ገቢ ያገኘው በማምረቻ ሼዶችና በለማ መሬት ኪራይ፤ ለመኖሪያ ቤቶች ከሚያገለግሉ አፓርትመንቶች እንዲሁም ከህንፃዎች ኪራይ እና ከተለያዩ የገቢ ማግኛ መንገዶች መሆኑ ተመላክቷል። 

ኮርፖሬሽኑ ካገኘው ከ992 ሚሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ውስጥ ከ244 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ በማግኘት አበረታች አፈፃፀም ማስመዝገቡ ነው በመድረኩ የተገለፀው። 

የኮርፖሬሽኑ የገቢ እና የትርፍ አፈፃፀሞች ውጤታማ እንዲሆኑ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና፤ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት እንዲሁም የተለያዩ ተጨማሪ ገቢ ማግኛ መንገዶች በየደረጃው  አበርክቶ እንዳላቸው ተጠቁሟል። 

IPDC earned more than 992 million birr in the first six months of 2016 fiscal year 

It is stated that Industrial Parks Development Corporation earned more than 992 million birr in the first six months of the 2016 fiscal year. 

This was revealed at IPDC's 6 month plan review event of the current fiscal year in Dire Dawa. 

The corporation earned this income through the rental of production sheds and service land, rental of apartments and commercial buildings used for housing and from different ways of generating addition income. 

It was also stated in the event that IPDC has scored impressive performance by earning a profit of more than 244 million birr out of the total income of 992 million birr. 

Industrial Parks and Dire Dawa Free Trade Zone, Industrial projects Service ( IPS ) as well as various ways ( projects ) of generating additional income have contributed at every level for the corporation's effective revenue and profit performance.

#Invest_In_Zero_Waiting_Time_Bureaucracy