• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 9 months, 3 weeks ago
  • 553 Views

ዋና ስራ አስፈፃሚው ለቻይና ኤምባሲና ለአምባሳደሩ ያቀረቡት ምስጋና

ዋና ስራ አስፈፃሚው በኢትዮጵያ ለቻይና ኤምባሲና ለአምባሳደር ዢኦ ምስጋናቸውን አቀረቡ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በኢትዮጵያ ለቻይና አምባሳደር ዢኦ ዥዩአን እና ለኤምባሲው ምስጋናቸውን አቀረቡ።

ዋና ስራ አስፈፃሚው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር የሆኑት ዢኦ ዥዩአን ኢትዮጵያ እና ቻይና በኢንቨስትመንት ያላቸው የጠነከረ ግንኙነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እያደረጉ ላሉት ያልተቋረጠ ጥረት ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

አክለውም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገንብቶ በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና በተለይም በፋርማሲዩቲካል እና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ በቀጣይም በመሰማራት በኢንቨስትመንት ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያሳድጉ ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ አክሊሉ ከአምባሳደሩ ጋር የተወያዩትና ይህን መልዕክት ያስተላለፉት በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ክትባቶችን ለማምረት ለሚያስችል ግዙፍ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ ከተቀመጠበት ፕሮግራም ጎን ለጎን ነው።

IPDC CEO thanked Chinese Embassy in Ethiopia and It's Ambassador Zhao

Industrial Parks Development Corporation CEO, expressed his gratitude to the Chinese Ambassador Zhao Zhiyuan and the Embassy in Ethiopia.

In a message posted on his official social media page, IPDC CEO Aklilu Tadesse stated that Zhao Zhiyuan, the Chinese ambassador to Ethiopia, deserves warm appreciation for his unwavering commitment to strengthen the strong investment relationship between Ethiopia and China.

Finally He called up on Chinese investors to increase their participation in investment at

Industrial Parks and Free Trade Zone that Industrial Parks Development Corporation has built, especially in the pharmaceutical and agro-processing sectors.

Mr. Aklilu discussed with the ambassador and conveyed this message on the sidelines of the program where the foundation stone of a huge project to produce vaccines was laid in Kilinto Industrial Park.

#Invest_In_Zero_Waiting_Time_Bureaucracy