• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 9 months ago
  • 264 Views

የቻይና የኢንቨስትመንት ልዑክ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ

ከቻይና ሀገር የመጣ የኢንቨስትመንት ልዑክ ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኘ

ከቻይና ከጂሊን ግዛት እና ፉያንግ አስተዳደር የመጣና ከተለያዩ አምራች ኩባንያዎች የተወጣጣ የልዑክ ቡድን ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን ተመልክቷል

ልዑክ ቡድኑ የጂሊን ግዛት የቋሚ ኮሚቴ ምክትል ፅሀፊ በሆኑት ፋን ፣ የፉያንግ አስተዳደር ምክትል ሴክረተሪ ጄኔራል በሆኑት ዋንግ ፈሂሁ እንዲሁም የኢትዮጵያ ቻይና የወዳጅነት እና ትብብር ኮሚቴ ሊቀመንበር በሆኑት ቤቲ ዙ የተመራ ሲሆን በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኙ አምራች ኩባንያዎችን ጎብኝተዋል፡፡

የልዑክ ቡድኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀጋዬ ዘካሪያስ ተቀብለው ያስጎበኙ ሲሆን ኮርፖሬሽኑ ያዘጋጀውን የኢንቨስትመንት አማራጮች፤ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም ማበረታቻዎችን ጨምረው ለልዑኩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ልዑኩ በቀረበለት ዝርዝር  መረጃ ላይ ላቀረበው ጥያቄዎች ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በቀጣይ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

An investment delegation from China visited Bole Limi Industrial Park

A delegation from China's Jilin Province and Fuyang Administration and various manufacturing companies visited Bole Lemi Industrial Park.

The delegation was led by Fan, the deputy secretary of the Standing Committee of Jilin Province, Wang Fehihu, the deputy secretary general of the Fuyang Administration, and Betty Zhu, the chairman of the Ethiopia-China Friendship and Cooperation Committee, and visited the manufacturing companies in Bole Limi Industrial Park.

IPDC's Industrial Parks Development division
Deputy CEO Tsegaye Zakarias, welcomed and toured the delegation and informed investment options, infrastructure as well as incentives prepared by the corporation for investors.

An explanation was given to the questions that the delegates made on the detailed information provided, and there was a discussion about the issues that could be worked in cooperation in the future.