• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 9 months, 1 week ago
  • 279 Views

የብራዚል ልዑክ የኢንዱስትሪ ፓርክ ጉብኝት

በፓርኩ የተመለከትነው መሰረተ ልማትና የአገልግሎት አሰጣጥ ለቀጣይ የጋራ ስራ የሚያነሳሳ ነው - አምባሳደር አሌክስ

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተመለከትነው እንግዳ አቀባበልና የአገልግሎት አሰጣጥ ለቀጣይ የጋራ ስራ የሚያነሳሳ ነው ሲሉ የብራዚል የንግድ፤ ኢንቨስትመንትና አግሪካልቸር ዳይሬክተር አምባሳደር አሌክስ ጂያኮሜሊ ገለፁ።

አምባሳደሩ ከብራዚል የተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት ከተወጣጡ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የስራ እንቅስቃሴን ተዟዙረው ተመልክተዋል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ልዑኩን ተቀብለው ኢንዱስትሪ ፓርኩን ያስጎበኙ ሲሆን ያሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮችና የፓርኩን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በዝርዝር በማስረዳት ኮርፖሬሽኑ የብራዚል ባለሀብቶች ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብተው እንዲያመርቱ እንዲሁም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ አምራች ኩባንያዎች የብራዚልን ገበያ መጠቀም እንዲችሉ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አሳውቀዋል።

በኢንዱስትሪ ፓርኩ የተመለከቱት እንቅስቃሴ በቀጣይ በጋራ ስራዎችን ለመስራት አስቻይ ሁኔታ መሆኑን የጠቆሙት ልዑኩን የመሩት አምባሳደር አሌክስ ቀጣይ ስራዎች ወደ መሬት በሚወርዱበት አካሄድ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በቅርበትና በትብብር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

ለልዑኩ አጠቃላይ ኮርፖሬሽኑን፤ ሁሉንም ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሁም ነፃ ንግድ ቀጠናን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

The infrastructure and service delivery we have seen in the park is a motivation for further cooperation - Ambassador Alex

The infrastructure and service delivery we have seen in Bole Lemi Industrial Park is a motivation for further cooperation, said Director of Investments and Agriculture Ambassador Alex Giacomelli.

The ambassador toured Bolemi Industrial Park with officials from various public and private institutions in Brazil.

The CEO of the corporation Aklilu Tadesse received the delegation and toured the industrial park and explained the available investment options and the overall activities of the park in detail. And announced that works are being done to enable Brazilian investors to enter and produce in industrial parks and that manufacturing companies in industrial parks can use the Brazilian market.

Ambassador Alex, who led the delegation, pointed out that the activity seen at the industrial park is a possibility for future cooperation and confirmed that they will work closely and cooperatively with IPDC in the way that next activities come down to the ground.

Current information related to all industrial parks and free trade zones were presented and discussed with the delegates.