• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 9 months, 1 week ago
  • 339 Views

የጃፓን ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለኢንቨስትመንት ተመራጭ መሆናቸውን የጃፓን ባለሀብቶች ገለፁ

በኢትዮ-ጃፓን የኢንቨስትመንት ፎረም የተሳተፉ የጃፓን ባለሀብቶች እና የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚተዳደሩት የቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ጉብኝት አድርገዋል።

የልዑካን ቡድኑ በጉብኝታቸውም የፓርኮቹን መሰረተ ልማት ፤ ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ እንዲሁም የባለሀብቶችን ተሳትፎ የተመለከቱ ሲሆን በፓርኮቹ ኢንቨስት ቢያደርጉ ስለሚያገኟቸው የኢንቨስትመንት አስቻይ ሁኔታዎችና ማበረታቻዎች ዙሪያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

በኮርፖሬሽኑ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን እና ማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘመን ጁነዲን በኢትዮጵያ እና በጃፓን መካከል የረጅም ጊዜ ወዳጅነት ቢኖርም በኮርፖሬሽኑ ስር በሚተዳደሩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የጃፓን ባለሀብቶች ያላቸው ተሳትፎ እንደ ግንኙነቱ ግዝፈት አለመሆኑን ጠቅሰው ኮርፖሬሽኑ ይህንን ለመቀየርና ባለሀብቶቹን ለማስተናገድ ከምጊዜውም በላይ ዝግጁ ነው ብለዋል።

አቶ ዘመን በተጨማሪም የጃፓን ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በተለይም በማኑፋክቸሪንግ እንዲሰማሩ የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸውንና በቀጣይም በፓርኮች ያለውን የጃፓናውያን ባለሀብቶች ተሳትፎ ለማሳደግ ኮርፖሬሽኑ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በጃፓን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የጃፓን ባለሀብቶች የልዑካን ቡድንን የመሩት የኢንስፓየር አፍሪካ አሶሴሽን ዳይሬክተር ያማጉቺ ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች በመሰረተ ልማት የተሟሉና ፤ ምቹ የስራ ከባቢ ዉስጥ መዘጋጀታቸውን ገልፀው የጃፓን ባለሀብቶች ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ባለሀብቶቹን የመለየት ስራዎችን አጠናክረው እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

Ethiopian industrial parks are suitable for investment - Japanese Investors

Japanese investors and various officials who participated in the Ethio-Japan Investment Forum visited Bole Lemi and Kilinto Industrial Parks managed by the Industrial Parks Development Corporation.

The delegation visited the infrastructure of the parks, looked at the current activity and the participation of investors, and they were informed about the possible investment conditions and incentives that they will get if they invest in the parks.

IPDC's Investment Promotion and Marketing Deputy CEO, Mr. Zemen Junedin, mentioned that despite the long-term friendship between Ethiopia and Japan, the participation of Japanese investors in the industrial parks under the corporation is not as important as the relationship. He said that the corporation is ready more than ever to change this and accommodate the investors.

Mr. Zemen also stated that preparations have been made to allow Japanese investors to engage in various investment sectors, especially in manufacturing, and that the Corporation is working with the Ministry of Foreign Affairs and the Ethiopian Embassy in Japan to further increase the participation of Japanese investors in the parks.

The director of Inspire Africa Association, Yamaguchi, who led the delegation of Japanese investors, said that the industrial parks are equipped with infrastructure for investors who want to engage in the manufacturing sector; He stated that they are prepared to identify the investors so that they can come in and invest.