• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 7 months, 3 weeks ago
  • 230 Views

ኮርፖሬሽኑ የጃፓን ባለሀብቶችን ለመቀበል ያለው ዝግጁነት

ኮርፖሬሽኑ የጃፓን ኢንቨስተሮችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ከምንግዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑ ተገለፀ 

ይህ የተገለፀው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ከ10 በላይ የሆኑ የጃፓን ኢንቨስትመንት ልኡክ የተሳተፉበትና በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮ-ጃፓን የቢዝነስ ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ነዉ።

ዋና ስራ አስፈፃሚው በመልዕክታቸው 90 ዓመታትን ከተሻገረው ከኢትዮ - ጃፓን ግንኙነት አንፃር ያለው የኢንቨስትመንት ግንኙነት ሳሳ ያለ መሆኑን አስታውሰው ይህንንም ለማጠናከርና በኢንዱስትሪ ፓርኮች የጃፓን ኢንቨስተሮችን ለማስተናገድ ያለው ዝግጁነት ከምንግዜውም ከፍ ያለ መሆኑን ገልፀዋል። 

አክለውም ኮርፖሬሽኑ ከፖሊሲ ጀምሮ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ እንዲሁም ሌሎች አሰራሮች ላይ ያደረገው ሪፎርም ለዚሁ ዝግጁነት ማሳያ መሆኑን አሳውቀዋል። 

በመድረኩ አጠቃላይ ኮርፖሬሽኑ እና ኢንዱስትሪ ፓርኮችን እንዲሁም በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ያሉ አጠቃላይ የኢንሸስትመንት እድሎችና፤ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም ማበረታቻዎች ለልዑክ ቡድኑና ለታዳሚያን ቀርበዋል። 

ልዑኩ በቀጣይም በአዲስ አበባ የሚገኙትን ቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።

'IPDC is ready more than ever to Welcome Japanese investors' IPDC CEO

This was stated at the Ethio-Japan Business Investment Forum in Addis Ababa, where IPDC and more than 10 Japanese investment delegations participated.

In his message, IPDC CEO Aklilu Tadesse reminded that the investment relationship between Ethio-Japan, which has crossed 90 years, is still weak and he expressed that the readiness to strengthen this relationship and host Japanese investors in industrial parks is higher than ever.

He added that the corporation's reforms in service delivery and other procedures, starting from policy, are an indication of its readiness.

General investment opportunities in the corporation's industrial parks as well as the Free Trade Zone of Dredawa and Infrastructure plus incentives were also presented to the delegation. 

The delegation is expected to visit Bole Lemi and Kilinto Industrial Parks in Addis Ababa.