ኮርፖሬሽኑ የሚሳተፍበትና ከ10 በላይ የሚሆኑ የጃፓን ኩባንያዎችና ባለሀብቶች የሚሳተፉበት የቢዝነስ ፎረም ነገ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሚሳተፍበትና ከጃፓን የተወጣጡ ከ10 በላይ የሚሆኑ የጃፓን ኩባንያዎችና ባለሀብቶች የሚሳተፉበት የቢዝነስ ፎረም ነገ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ታውቋል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲን ለማሳደግ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል በተለያዩ አገራት የሚገኙ የውጭ ባለሀብቶችን በሚሲዮኖች በኩል በመመልመል ወደ አገር በማስገባት በኢንቨስትመንት እንዲሳተፉ ፎረሞችን በማዘጋጃት ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
ከጃፓን የተወጣጡ ኩባንያዎችና ባለሀብቶች ትልቅ አቅም ያላቸው በመሆኑ በአገሪቱ በሚመቻችላው የኢንቨስትመንት አማራጮች በመሳተፍ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን የኢንዱትስሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንም በመድረኩ ተሳታፊ ይሆናል፡፡
ባለሀብቶቹና ኩባንያዎቹ በቆይታቸው ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸዉ የተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የኢንቨስትመንት ጉብኝት እንደሚያደርጉ እንዲሁም ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በመመልከት ከኮርፖሬሽኑ የስራ ኃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።