• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 7 months, 3 weeks ago
  • 251 Views

በሰው ሀይል ልማት ላይ በጋራ ለመስራት የተደረገው ውይይት

"በኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ዋነኛ አቅምና ተዋናይ የሆነዉ  የሰዉ ሃይል ልማት ላይ በትብብር መስራት ያስፈልጋል" - አክሊሉ ታደሰ 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከኢፌዴሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይቷል። 

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና ሌሎች የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ከኢንስቲትዩቱ
ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) እና ሌሎች
ኃላፊዎች ጋር በሰው ሀይል ልማት ዙሪያ ዝርዝር ውይይት አካሂደዋል። 

በውይይቱም ሁለቱ ተቋማት በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ጥልቅ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በውይይቱም በሰው ሀይል ልማት፤ በስልጠና፤ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በጋራ ለመስራት ከስምምነት ተደርሷል። 

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ዋነኛ አቅምና ተዋናይ የሆነዉ  የሰዉ ሃይል ልማት ላይ በትብብር ተቀራርቦ መስራት መስራት አገሪቷ ለምታስበው ኢንዱስትሪያላይዜሽን እውን መሆን ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ አንስተዋል።

የቴክኒክ እና ሙያ ዘርፍ ዘርፈ ብዙ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ በተለይም የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ በመደገፍ፤ ግብዓት በመሆንና የስራ እድል ፈጠራን በማሳደግ ረገድ የማይተካ ሚና እንደሚኖረው በመድረኩ ተገልጿል።