• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 7 months, 3 weeks ago
  • 248 Views

የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ መልዕክት

የውጭ እና የአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ ማድረግ ይገባል - ሙፈሪሃት ካሚል

የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የውጪና የአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ በማድረግ ለሰራተኛው እና አሰሪው ምቹ የሆኑ የስራ ከባቢዎችን ለመፍጠር በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

ሚኒስትሯ ይህን የተናገሩት ኢትዮጵያ የዓለም የስራ ድርጅት አባል የሆነችበት 100ኛ ዓመት በተከበረበት ወቅት ነው።

በመድረኩ ሚኒስትሯ አሰሪና ሰራተኛው ተለያይቶ የሚፈለገውን ስኬት ማስመዝገብ እንደማይቻልና የሁለቱ ግንኙነት ከስራው ዓለም ያለፈም መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

ዛሬ ላይ ለመድረስ ብዙ ስራዎች መሰራቱን ያስታወሱት ሚኒስትሯ ነገር ግን አሁን የበለጠ ስኬት የሚያስፈልግበት ወቅት መሆኑ ታውቆ በጋራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በተለይም የግሉን ዘርፍ በማገዝ ለሰራተኛው የሚያስፈልጉ መሠረታዊ የሆኑ ችግሮች በመፍታት እና አካታች የሆነ የስራ እንቅስቃሴን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በ10 ዓመቱ የልማት እቅድ መሠረት የግል ዘርፉን ተሳትፎ ማሳደግ መቻሉን እና ሰራተኛው ከስራ ገበታው እንዳይፈናቀል ለማድረግ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን ሚኒስትሯ አስታውሰዋል።

በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት አስተባባሪ ራሚስ አላካባር (ዶ/ር) በበኩላቸው ኢትዮጵያ እየተገበረች ለምትገኘው የ10 ዓመት የልማት እቅድ ስኬት ሰፊ የስራ እድል ፈጠራዎች ፍትሐዊ የስራ ተደራሽነት እና የኢንዱስትሪ ሰላም ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የስራ ድርጅት አባል መሆኗ እየተመዘገበ ላለው የልማት ስራዎች እና የስራ እድል ፈጠራዎች ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ደግሞ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፌዴሬሽን ኮንፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን አሶሴሽን ተወካዮች ተናግረዋል።