• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 10 months ago
  • 322 Views

አምራቾች የተለያዩ የገበያ አማራጮችን እየተጠቀሙ መሆኑ

አምራቾች የተለያዩ የገበያ አማራጮችን በማፈላለግ ምርቶቻቸውን ለአለም ገበያ እያቀረቡ መሆኑ ተገለፀ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ አምራቾች የተለያዩ የአለም የገበያ አማራጮችን በመፈለግ የተለያዩ ምርቶቻቸውን በተለያዩ የአለም አገራት እየላኩ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ የተገለፀው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የማርኬቲንግ፤ ቢዝነስና ኢንቨስትመንት ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘመን ጁነዲን በአዲስ ኢንዱስትሪ መንደር እያመረቱ የሚገኙ ኩባንያዎችን ተዟዙረው በተመለከቱበት ወቅት ነው።

ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው ባደረጉት ምልከታ የኩባንያዎቹን የስራ ሀላፊዎች ያነጋገሩ ሲሆን ኃላፊዎቹም የአጎዋ ተጠቃሚነት አሁን ላይ ባይኖርም ጠንካራ አማራጭ ገበያዎችን በማፈላለግ ምርቶቻቸውን ለአለም ገበያ እያቀረቡ መሆኑን አሳውቀዋል።

በኢንዱስትሪ መንደሩ ውስጥ በምርት ሂደት ላይ ከሚገኙ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ፒታርድስ ማኑፋክቸሪንግ የቆዳ ምርቶችን በማምረት ላይ የተሰማራ ኩባንያ የአጎዋ ፤ የኮቪድ እንዲሁም የውጪ ምንዛሪ ጫናን በመቋቋም እየሰራ ሲሆን በአሁን ሰዓት ምርቶቹን ለዩናይትድ ኪንግደም ፤ ለጃፓን፤ ለኔዘርላንድና ለደቡብ አፍሪካ እያቀረበ መሆኑንና የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ እቅድ በማዘጋጀት ላይ መሆኑንም ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ ፀደኒያ መክብብ ገልፃለች።

አቶ ዘመን በበኩላቸው የኩባንያዎቹን ጠንካራ እንቅስቃሴ አድንቀው ተጨማሪ አማራጭ ገበያዎችን በማፈላለግ፤ የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን በማጠናከርና ተጨማሪ የኢንቨስትመንት ቦታዎችን በማቅረብ አምራቾችን ለመደገፍ ኮርፖሬሽኑ የጀመረዉን የሪፎርም ተግባር አጠናክሮ ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቀዋል ፤ ባለፈው አንድ አመት ኮርፖሬሽኑ በተለያዩ ፓርኮች ለሚመረቱ ምርቶች ተጨማሪ ገበያ የማፈላለግ ተግባራትን በስፋት መከወኑን ገልፀው ይህም በገበያ አማራጭና ብዝሀነት ላይ አበረታች ዉጤት እየታየበት መምጣቱን አንስተዋል ።