• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 10 months, 3 weeks ago
  • 359 Views

“ACT Excellence” የተሰኘው የኮርፖሬሽኑ አዲስ ፕሮግራም

ኮርፖሬሽኑ “ACT Excellence” የተሰኘ ፕሮግራሙን በይፋ ጀመረ

በዛሬው እለት የተጀመረው “Act Excellence” የተሰኘው የኮርፖሬሽኑ አዲስ ፕሮግራም ኮርፖሬሽኑ ከጀመራቸው በርካታ ሪፎርሞች መካከል አንዱ ሲሆን በዋናነት የኮርፖሬሽኑን ባለሞያዎችና ኃላፊዎች በዕውቀትና በአለም ዓቀፍ ልምድ የበቁ ፈጣንና ጥራት ያለው አገልግሎት የሚሰጡ ማድረግ እንደሆነ ተገልጿል ፡፡ 

የኮርፖሬሽኑ የሰው ሃብት ልማት ላይ አተኩሮ የሚሰራው ይህ ፕሮግራም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የያዘውን ከፍተኛ አገራዊና ተቋማዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት የስራ ኃላፊዎችንና ፈፃሚዎችን አቅምና ብቃት አለም ከደረሰበት የላቀ ደረጃ ማድረስ ያለመ ሲሆን በተግባር ላይ የሚገኙ ጉድለቶችን የሚሞላ ተግባር ነክ ስልጠና እና አለም አቀፍ የተሞክሮ ልውውጥ በማድረግ  ባለሙያና ሃላፊዎችን ማብቃትን የሚያካትት ነው ተብሏል፡፡

በዚሁ መሰረት በዛሬው እለት ከኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት እና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች የተወጣጡ ፈፃሚዎች ወደ ቻይና ተጉዘው ለሚወስዱት ስልጠና ከኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ጋር ውይይት በማድረግ የክንውን አቅጣጫዎችን ተቀብለዋል። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው እንዲህ ያሉ የባለሞያዎችና የኃላፊዎችን አቅም የሚያጎለብቱ የአጭር እና የመካከለኛ እንዲሁም የረጅም ጊዜ የትምህርትና የስልጠና እድሎችን በማመቻቸት የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች እንደሚጠናከሩ ያረጋገጡ ሲሆን ፕሮግራሙን “ACT Excellence” በማለት መሰየሙን ይፋ አድርገዋል፡፡