• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 8 months, 1 week ago
  • 297 Views

ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተደረገበት ኩባንያ

ከ 15 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተደረገበት ኩባንያ ተመርቆ ስራ ጀመረ

በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ3000 ስ.ሜ የማምረቻ ሼድ ላይ ያረፈውና ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተደረገበት የፕላስቲክ ቧንቧና መሰል የግንባታ ግብዓቶችን የሚያመርት ኢ ዜድ ኤም የተባለ ኩባንያ ተመርቆ ወደ ስራ ገብቷል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከአዳማ ከተማ ክቡር ከንቲባ ኦቦ ሀይሉ ጀልዴ እና ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በመሆን ኩባንያውን መርቀው በመክፈት ስራ አስጀምረዋል።

ኩባንያው  "ኢ ዜድ ኤም ትሬድ ኤንድ ኢንቨስትመንት" የሚሰኝ ሲሆን "ሪፎ ኢንተርናሽናል ከተሰኘው" የቻይናው የፕላስቲክ ቧንቧ አምራችና አቅራቢ ኩባንያ ጋር በሽርክና ተቋቁሞ በዘርፉ የሚስተዋለውን የአቅርቦት እጥረት ለመፍታትና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት አላማ በማድረግ ከ600 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር ይሆናል።

አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኮርፖሬሽኑ ከሚያስተዳድራቸው ግዙፍ 13 የኢንቨስትመንት ማዕከላት አንዱ ሲሆን በፓርኩ ውስጥ የተገነቡ 19 የማምረቻ ሼዶች በጃፓን፣ በቻይና ፣ በሕንድ፣ በኖርዌይ፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እንዲሁም በአገር ውስጥ ኩባንያዎች ተይዘው ከ8500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል።

A company that has More than 15 million USD capital has started operation

A company called E Z M, a manufacturer of plastic pipes and similar construction materials, which has took a 3000 s.m production shed at Adama Industrial Park and has spent more than 15 million USD, has been inagurated today . 

IPDC CEO Aklilu Tadesse, together with tAdama city Mayor Obo Hailu Jelde and other higher officials inaugurated the company.

The company named "EZM Trade and Investment" has established a partnership with "Rifo International", a Chinese plastic pipe manufacturer and supplier, with the aim of solving the shortage of supply in the sector and replacing imported products and will create employment opportunities for more than 600 citizens.

Adama Industrial Park is one of the huge 13 investment hubs managed by the IPDC, and the 19 production sheds built in the park have been occupied by Japan, China, India, Norway, United Arab Emirates and local companies, creating employment opportunities for more than 8500 citizens.