• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 8 months, 1 week ago
  • 314 Views

የኮርፖሬሽኑ የመጀመሪያ ሩብ አመት የዝግጅት ስራዎች አበረታች መሆን

" የኮርፖሬሽኑ የመጀመሪያ ሩብ አመት የዝግጅት ስራዎች አበረታች ናቸው " የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዝግጅት ስራዎች ክንዋኔ አበረታች መሆኑን የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ኃይለሚካኤል ገልፀዋል። 

የኮርፖሬሽኑ የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዝግጅት ስራዎች በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር እየተገመገመ ሲገኝ በዝርዝር አፈፃፀሞች ላይም ከኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና የማኔጅመንት አባላት ጋር በሐዋሳ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል። 

አስተዳደሩ ለኮርፖሬሽኑ ቀጣይ ስራዎችና ውጤታማነት ድጋፍ እንደሚያደርግም በመድረኩ የተገለፀ ሲሆን የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወቅታዊ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ በፓርኩ ከሚገኙ አምራቾች መካከ ጄፒ ቴክስታይል እና ኢንዶቺን አፓረል የተሰኙ ሁለት  ኩባንያዎች ተጎብኝተዋል። 

በጉብኝቱም ኩባንያዎቹ በስራ እስል ፈጠራ፤ ተኪ ምርትን በማምረት፤ እንዲሁም በቴክኔሎጂና እውቀት ሽግግር ላይ ያላቸው ውጤታማነት አበረታች መሆኑ ተገልጿል።