• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 11 months, 2 weeks ago
  • 352 Views

የኢትዮ-ኮሪያ ቴክስታይል ቴክኖ ፓርክ ፕሮጀክት

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኢትዮ-ኮሪያ ቴክስታይል ቴክኖ ፓርክ ፕሮጀክት ተመረቀ

በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ካንግ ሴኪዮሄ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ፕሮጀክቱን መርቀው ከፍተዋል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ወቅት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ በደምና አጥንት የተሳሰረ ረጅም ዓመት የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን አስታውሰው ይህ ግንኙነት በዚህ መሰል ፕሮጀክቶች መጠናከሩ ለቀጣይ ግንኙነት ግብዓት መሆኑን አውስተዋል።

ደቡብ ኮሪያ በዘርፉ የደረሰችበትን ውጤታማነት በኢትዮጵያ በአጭር ግዜ እውን ለማድረግ ይህ ፕሮጀክት ያለው ሚና ጉልህ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን መሰል ሌሎች ፕሮጀክቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በትብብር ይሰራል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ካንግ ሴኪዮሄ በበኩላቸው የቴክኖ ፓርክ ፕሮጀክት ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ ያላቸውን ግንኙነት የሚያጠናክርና የወደፊት የአብሮነት ጉዞ ማሳያ መሆኑን ገልፀው ደቡብ ኮሪያ በሌሎች መሰል ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኗን አሳውቀዋል።

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በዛሬው እለት በይፋ የተመረቀው የኢትዮ-ኮሪያ ቴክስታይል ቴክኖ ፓርክ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚመረቱ የቴክስታይል ምርቶች የሚፈተሹበት፤ ዲዛይን ላይ ለሰራተኞች የተግባርና ቴክኒካል ስልጠና የሚሰጥበት፤ እና በረጅም ግዜ እቅድ ለአምራቾች አለም አቀፍ ገበያ የማፈላለግ ስራዎች እንደሚከናወንበት ተገልጿል።

The Ethio-Korea Textile Techno Park project was officially inaugurated at Bole Limi Industrial Park

Ambassador of South Korea to Ethiopia Kang Seokhee and Industrial Parks Development Corporation CEO Aklilu Tadesse inaugurated the project.

During the inauguration ceremony, IPDC CEO, Aklilu Tadesse, reminded that Ethiopia and South Korea have a long-standing strong relationship bound by blood and bones and noted that the strengthening of this relationship through projects like this is a resource for future relations.

The CEO added that the role of this project is significant in order to realize the effectiveness of South Korea in the field in Ethiopia in a short period of time.

Kang Seokhee, South Korea's ambassador to Ethiopia, said that the Techno Park project will strengthen the relationship between Ethiopia and South Korea and is a sign of future cooperation. He strongly added that, South Korea is ready to work together with Ethiopia in other similar fields of collaboration.

The Ethio-Korea Textile Techno Park, which was officially inaugurated today at Bole Limi Industrial Park, is where the textile products produced in the industrial parks will be tested; where practical and technical training is given to employees in design; And in the long-term plan, it is stated that the activities of finding international market for the producers will be carried out.