የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከ2 የስኳር ፋብሪካዎች ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ
የውል ስምምነቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የትራንስፎርሜሽንና ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም ከተማ ከከሰም እና ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ስራ አስኪያጆች ጋር ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ለስኳር ፋብሪካዎቹ የንብረት ትመና በማድረግ እና የፋይናንስ ድጋፍ የሚያገኙበትን የጥናትና ምርምር ስራ በማከናወን ወደ ተሻለ ምርታማነት ለማሸጋገር ያለመ መሆኑን ተገልጿል፡፡
የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት በጥናትና ማማከር ላለፉት 40 ዓመታት በላይ የተለያዩ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን እውን ያደረገ ሲሆን ከዚህ ቀደም ከ3 ግዙፍ የስኳር ፋብሪካዎችና ከሌሎችም ተቋማትና ፕሮጀክቶች ጋር የጥናትና ምርምር እንዲሁም የማማከር ስራዎችን ለማከናወን የውል ስምምነት መፈራረሙ አይዘነጋም፡፡