• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 3 months ago
  • 1161 Views

#Development_story

#Development_story

የማምረቻ ሼዶችን እና የለሙ መሬቶችን ከኮርፖሬሽኑ የተረከቡ አምራች ኩባንያዎችና ባለሀብቶች ወደ ስራ እየገቡ ነው።

ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር የውል ስምምነት ተፈራርመው የማምረቻ ሼዶችን እና የለሙ መሬቶችን የተረከቡ አምራች ኩባንያዎችና ባለሀብቶች የግንባታ፤ የቅድመ ኦፕሬሽን እና የማሽን ገጠማ ስራዎቻቸውን እያጠናቀቁ እንደሚገኙ የኮርፖሬሽኑ የማርኬቲንግና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘመን ጁነዲን ገልፀዋል።

ኃላፊው ከ14.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት በማድረግ በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ 3ሺ ሜ.ስ ማምረቻ ሼድ የተረከበው ኢዘም ትሬድ ኤንድ ኢንቨስትመንት በአሁን ሰዓት ማምረቻ ማሽነሪዎቹን ገጣጥሞ እያጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡም ሙሉ ለሙሉ ስራ የሚጀምር ይሆናል ብለዋል።

ኒልኮን ኤሌክትሪክ ማኑፋክቸሪንግ የተሰኘ ሌላ ኩባንያ ከ11 ሚሊዮን ዶላር በላይ በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ኢንቨስት በማድረግ 3ሺ ሜ.ስ የማምረቻ ሼድ የወሰደ ሲሆን አሁን ላይ ማሽነሪዎችን በማስመጣት በመገጣጠም ላይ እንደሚገኝና በቅርቡ ወደ ስራ የሚገባው ሌላኛው ኩባንያ መሆኑን ኃላፊው አክለዋል።

ሁለቱ ኩባንያዎች በሙሉ አቅማቸው በቅርቡ ስራ ሲጀምሩ ከ800 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥሩ ይሆናል።