• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year ago
  • 368 Views

የማላዊ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ልዑክ

በማላዊ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የተመራ የልዑካን ቡድን ከኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያየ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የትራንስፎርሜሽንና ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም ከተማ በማላዊ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የተመራ የልዑካን ቡድን አባላትን በኮርፖሬሽኑ ጽ/ቤት ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በውይይታቸው በማላዊ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለማቋቋም የኢትዮጵያን ኢንዱስትሪ ፓርኮችን የማልማትና የማስተዳደር ልምድና በማማከርና የአዋጭነት ጥናት በመስራት የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት በዘርፉ ስለሚያደርግላቸው ድጋፍ በዝርዝር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ በኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን ተሞክሮ ከመቅሰም ባለፈ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በአብሮነት መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት የተደረሰ ሲሆን በተለይም የአዋጭነት ጥናትና ማማከር ላይ ያለውን ልምድ ተጠቅሞ በአጭር ጊዜ በማላዊ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለመገንባት እንዲያግዛቸው ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በቆይታቸው የሃዋሳ እና ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ የሚጎበኙ ሲሆን በጉብኝታቸውም በስራ እድል ፈጠራ፣ በአረንጓዴ አሻራ ልማትና በአንድ ማዕከል አገልግሎት በፓርኮቹ ያለውን ተሞክሮ ላይ ትኩረታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

A delegation led by high government officials of Malawi discussed issues that can be worked together with the services of industrial projects service

IPDC chief of staff Mr. Fitsum Ketema received and spoke to the members of the delegation led by high government officials of Malawi in his office.

In their discussion, the delegation discussed in detail the experience of developing and managing Ethiopia's industrial parks and the long-term experience of industrial projects service ( IPS ) in the sector by consulting and conducting feasibility studies to establish industrial parks in Malawi.

In the discussion, apart from learning about the experience of industrial parks in Ethiopia, a consensus was reached on the issues on which they can work together with the corporation. Additionally, they called on IPS to use its experience in feasibility studies and consulting to help them build industrial parks in Malawi in a short period of time.

The delegation will visit Hawassa and Bole Limi Industrial Parks and will focus on job creation, green legacy development and one stop service experience in the parks.