• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 4 months ago
  • 1065 Views

የስፔን የጨርቃጨርቅ አምራቾች በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ

አድቫንስ ግሩፕ ፕሮጀክትስ ኤንድ ቴክኖሎጂስ የተሰኘ የማኑፋክቸሪንግ አማካሪ ድርጅት የስፔን ባለሀብቶች በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገለፀ 

አማካሪ ድርጅቱ በጨርቃጨርቅና አልባሳት ምርት ላይ የተሰማራ የስፔን አምራች ኩባንያ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት የማድረግና የማምረት ፍላጎት እንዳለው ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አሳውቋል። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ከአማካሪ ድርጅቱ ባለቤት ሮቤርቶ ቶሎሳና ጋር በበይነ መረብ የተወያዩ ሲሆን በውይይቱም ኮርፖሬሽኑ እያከናወናቸው ስላሉ የሪፎርም ስራዎች፣ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ማበረታቻዎች እንዲሁም ሌሎች ዝርዝር ሀሳቦች ቀርበዋል። 

የአማካሪ ድርጅቱ ባለቤት የቀረበላቸውን ዝርዝር ኢንቨስትመንት ተኮር ሀሳብ አድንቀው የስፔኑ ኩባንያ በኢንቨስትመንቱ እንዲሰማራና ቅድመ ኢንቨስትመንት ስራዎችን እንዲያከናውን የተስማሙ ሲሆን በድርጅቱ በኩልም ኢንቨስትመንት ተኮር ጥያቄዎቻቸውን አንስተው ዝርዝር ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። 

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ኮርፖሬሽኑ ለኢንቨስትመንቱ መሳካት አስፈላጊውን ሁሉ እገዛዎችና የኢንቨስትመንት ክትትል እንደሚያደርግ ለአማካሪ ድርጅቱ ባለቤት አረጋግጠው በአፋጣኝ ወደ ስራ የሚገባበት አግባብ እንዲኖር ይሰራል ብለዋል። 

አማካሪ ድርጅቱ የሚያመጣው የስፔን አምራች ኩባንያ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሶስት የማምረቻ ሼዶችን በመውሰድ ቲሸርት፣ ሱሪ እና ጃኬቶችን የማምረት ፍላጎት ያላቸው ሲሆን ወደ ስራ ሲገባ በወር 225 ሺህ አልባሳትን የማምረት እቅድ ያለው ነው።

Advance Group Projects and Technologies S.L, a manufacturing consulting firm, stated that Spanish investors are interested in investing in Hawassa Industrial Park. 

The consulting firm has informed IPDC that a Spanish manufacturing company engaged in textile and clothing manufacturing is interested in investing and manufacturing in Hawassa Industrial Park. 

IPDC CEO, Aklilu Tadesse, and other officials discussed with Roberto Tolosana, the owner of the consulting firm, online, and in the discussion, the reform works, investment options and incentives, as well as other detailed investment related ideas were presented. 

The owner of the consulting firm appreciated the detailed investment-oriented proposal presented to them and agreed to let the Spanish company engage in the investment and carry out pre-investment activities. 

IPDC CEO, Aklilu Tadesse, assured the owner that IPDC will provide all the necessary assistance and investment followup for the success of the investment and will work to ensure that it can be put into work as soon as possible. 

The Spanish manufacturing company brought by the consulting firm is interested in producing t-shirts, trousers and jackets by taking three production sheds in Hawassa Industrial Park and plans to produce 225 thousand garments per month when it is operational.