ኮርፖሬሽኑና በኢትዮጵያ የህንድ ኤምባሲ በጋራ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና በኢትዮጵያ የህንድ ኤምባሲ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አዲሱ ማሞ እና ሌሎች ኃላፊዎች በኢትዮጵያ ከህንድ ኤምባሲ ሰከንድ ሴክረተሪ ቬንካታቻላም እና የንግድ አታሼ ራቪ ሻንካር ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱም በህንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ለረዥም ዓመታት የቆየውን ወዳጅነት በኢንቨስትመንት፣ በትምህርት፣ በስራ እድል እንዲሁም በባህል ትስስር አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የህንድ ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በመሰማራት በኢትዮጵያ የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ላይ ተሳትፎ በማድረግ በስራ እድል ፈጠራ ፤ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና የውጪ ምንዛሬ በማስገኘት በኩል ጉልህ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸው ተነስቷል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የህንድ ባለሀብቶችን ጨምሮ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስት ላደረጉ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ባለሀብቶች ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ ሁኔታ እየፈጠረ መሆኑም በውይይቱ ተገልጿል፡፡
በኢንዱስትሪ ፓርኮች በተለይም በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና የህንድ ባለሀብቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እንዲሁም በጋራ ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከስምምነት የተደረሰ ሲሆን የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞችን ተወዳዳሪ የሚያደርግ አጫጭር ስልጠናዎች እና የትምህርት እድሎች በህንድ ሀገር እንዲመቻች ለማድረግ በኤምባሲው እና በሰው ሀብት አስተዳደር መምሪያ በኩል መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
Issues has been discussed that IPDC and the Indian Embassy in Ethiopia can work together
Industrial Parks Development Corporation and the Indian Embassy in Ethiopia discussed various issues on which they can work together.
IPDC Deputy CEO, Addissu Mamo and other leaders discussed with Indian Embassy Second Secretary Venkatachalam and Commercial Attache Ravi Shankar in Ethiopia.
In the discussion, a consensus was reached on the issues that can be strengthened in terms of investment, education, job opportunities and cultural ties between India and Ethiopia, which has existed for many years.
Indian investors engaged in various investment sectors and participated in FDI in Ethiopia are playing a significant role through technology transfer and earning foreign currency.
It was also stated in the discussion that IPDC is creating a favorable investment environment for domestic and foreign investors who have invested in industrial parks, including Indian investors.
In industrial parks, especially in Dire Dawa Free Trade Zone, an agreement was reached on the issues that can be worked together to increase the participation of Indian investors, and the Embassy and IPDC Department of Human Resource Management reached an agreement to facilitate short trainings and educational opportunities for the corporation's employees in India.