• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 5 months ago
  • 984 Views

የፖርቹጋል ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና

የፖርቹጋል ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ኢንቨስት ማድረግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሚመራውና አዳዲስ ኢንቨስትመንት ስበት ላይ ያተኮረው ይህ ውይይት በፖርቹጋል ሊዝበን ከፖርቹጋል ትሬድ እና ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ሀላፊ አምባሳደር ክርስቲና ፑካሪንሆ ጋር ተካሂዷል።

በውይይቱም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ፤ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ እና የተለያዩ የኮርፖሬሽኑና ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የነፃ ንግድ ቀጠና ስራ አስኪያጆች ተሳትፈዋል።

በውይይት መድረኩ በኢትዮጵያ በተለይም በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ፤ ምቹ መሰረተ ልማቶችና የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በፖርቹጋል የሚገኙ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የተለያዩ ዘርፎች ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

ውይይቱ ከኢንቨስትመንት በተጨማሪ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በከተሞች መካከል ስላለው አዎንታዊ መስተጋብር ልምድና ተሞክሮ የሚወሰድበት መድረክ ነው ተብሏል።

ከቀናት በፊት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የተመራ ልዑክ በአዲስ አበባ የፓርቹጋል አምባሳደር የሆኑትን ሉዊዛ ፍራጎሶ አግኝተው በኢንቨስትመንትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ከስምምነት መድረሳቸው አይዘነጋም።

A discussion was held on the possible way that Portuguese investors can invest in industrial parks and Dire Dawa Free Trade Zone.

This discussion, led by IPDC and focused on investment attraction, was held in Lisbon, Portugal.

IPDC CEO, Aklilu Tadesse, and other senior officials as well as Dire Dawa City Mayor Keder Juhar, Hawassa City Mayor Assistant Professor Tsagaye Tuke and managers of various industrial parks participated in the discussion.

In the discussion, investment options, convenient infrastructure and investment incentives in Ethiopia, especially in industrial parks and the Dire Dawa Free Trade Zone, were presented and discussed, and investors in Portugal were

7 invited to invest in Ethiopia.

In addition to investment, the discussion is said to be a forum for sharing experiences and positive interactions between industrial parks and cities.

A few days ago, a delegation led by the IPDC CEO, Aklilu Tadese, met with the Portuguese ambassador in Addis Ababa, Luisa Fragoso, and reached an agreement to cooperate on investment and related issues.