
ሀገር አቀፍ የአቅራቢዎች ዝርዝር የፍላጎት መግለጫ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር IPDC-CDB/NCB/EOI-02/2018
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 326/2007 የተቋቋመ ዋና የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን ብቁ እና ልምድ ያላቸውን አቅራቢዎች በስትራቴጂካዊ አጋርነት መርጦ ማሰራት ይፈልጋል ።
ዓላማው፡የኮንስትራክሽን ልማት ቢዝነስ ብቁ የሆኑ አቅራቢዎችን በስትራቴጂካዊ አጋርነት የግዥ ስልት በመጠቀም ለ2 (ሁለት) ዓመታት ስራዎችን ፤ ዕቃዎችን፣ እና አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ አስተማማኝ ብቃት ያላቸውን አቅራቢዎች ቀድሞ በመለየት እና በዝርዝር በመያዝ የግዥ ቅልጥፍናን በማሻሻል፣ ተወዳዳሪ ዋጋን በመጠበቅ፣ ጥራትን በማረጋገጥ እና የአቅራቢዎችን አጋርነት በማጠናከር ግዥዎችን በመፈፀም የኮርፖሬሽናችንን ዓላማ ማሳካት ፡፡
2. ለተጫራቾች መመሪያ
• ጨረታ ማስረከቢያ ቀን ፡- እስከ የካቲት 1/2018 ዓ.ም ሰዓት ፡ 11፡00
• ጨረታ ማስረከቢያ አድራሻ ፡- የኮንስትራከሽን ልማት ቢዝነስ ቀበና- ከ ኬኒያ ኢንባሲ ፊት ለፊት ሀ ቤት ህንጻ 3ተኛ ፎቅ የኮንስትራክሽን ልማት ቢዝነስ ግዥ፡ንብረትና አቅርቦት አስተዳደር ክፍል
• የጨረታ ቋንቋ ፡ - ፕሮፖዛል በ እንግሊዘኛ መቅረብ አለበት
• የማብራሪያዎች ጥያቄዎች ፡- የማብራሪያ ጥያቄዎች ጨረታው ከመዘጋቱ 5 (አምስት) ቀናት በፊት ለኮ.ቢል. የ ኮርፖሬት ቢዝነስ ግዥ እና ንብረት አቅርቦት አስተዳደር ።
• ጨረታው የሚቀርብበት ፎርማት ፡- ተጫራቹ ለሚወዳደርበት እያንዳንዱ የጨረታ አይነት ለአንድ ምድብ አንድ ፕሮፖዛል በተለየ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከዚህ ቀደም ተመዝግበው መስፈርቱን በማሟላት በኮንስትራክሽኑ የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተያዙ አቅራቢዎች ካሉ በዚህ ውስጥ ተካተው የሚያዙ በመሆኑ በድጋሚ መመዝገብ አይጠበቅባቸውም፡፡
3. የጨረታ ሰነዱን ማዘጋጀት ያስፈለገበት ዝርዝር ዓላማ ፡-
• ለሚገዙ እቃዎች፣ ስራዎች እና አገልግሎቶች ብቃት ያላቸው እና አስተማማኝ አቅራቢዎች ዝርዝር በመያዝ ግዥዎችን መፈጸም ፤
• ተደጋጋሚ ጨረታዎችን በመቀነስ የግዥ ሂደቶችን ማቀላጠፍ ፤
• ተወዳዳሪ ዋጋን እና ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ጥቅም ማግኘት ፤
• በረጅም ጊዜ አጋርነት የአቅራቢዎች ግንኙነትና አስተዳደርን ማጠናከር ፤
• የግልጽነት፣ የፍትሃዊነት እና የተጠያቂነት ግዥ መርሆዎችን ማክበር እና ማሳደግ።
4. የሥራ ወሰን (Scope of work)
አቅራቢዎች በአባሪ ሀ ውስጥ ለተዘረዘሩት አንድ ወይም ከዚያ በላይ ምድቦች መወዳደር ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በተራ ቁጥር አምስት ላይ የተዘረዘሩትን የሟሟላት ግዴታ ይኖርባቸዋል።
5. ህጋዊነት እና የብቃት መስፈርቶች
ፍላጎት ያላቸው አቅራቢዎች የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ አለባቸው ፡-
• በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፤
• የቅርብ ጊዜ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፊኬት፤
• ላለፉት 3 (ሁለት) ዓመታት በውጭ ኦዲተር የተመሰከረ የሂሳብ እንቅስቃሴን ሪፖርቶች፤
• የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት፤
የ EGP (Electronic government procurement) ምዝገባ የምስክር ወረቀት
• በቅርብ 3 (ሶስት) ዓመታት የስራ አፈጻጸም የሚያሳይ ማረጋገጫ ፤
• የሚፈልጓቸውን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በሚፈለገው ጊዜ፣ ቦታ፣ ሁኔታ፣ መጠን እና ጥራት ለማቅረብ ፈቃደኛ እና ኃላፊነት ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ፤
• ለአምራች ድርጅት ፣ አስመጪ እና ጅምላ ነጋዴ (manufacturing Authorization)
• የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት (quality certificate)
• ዋስትና (warranty certificate)
7. የግምገማ ዘዴ (Evaluation Methodology)
በቴክኒካል ግምገማ ውስጥ ያሉትን መስፈርቶች "ያሟሉ" አቅራቢዎች ብቻ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ይካተታሉ ፡፡
8. የአቅራቢዎች ዝርዝር ቆይታ
በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመረጡት ለ2 ዓመታት ያገለግላሉ ። ድርጅቱ በአፈጻጸም ወይም በተገዥነት ጉዳዮች ላይ በመመስረት አቅራቢዎችን የማዘመን፣ የማገድ ወይም የማቋረጥ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
9. ውሎች እና ሁኔታዎች
• በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተት አሸናፊነትን ለመስጠት ዋስትና አይሰጥም ፤
• ድርጅቱ ምንም አይነት ምክንያት ሳይሰጥ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፤
• ድርጅቱ አጥጋቢ አፈጻጸም በማይኖርበት ጊዜ ስምምነቱን የማቋረጥ መብቱ የተጠበቀ ነው ፤
• አቅራቢዎች የአቅራቢውን የስነ-ምግባር ህግ (አባሪ ሐ) ማክበር አለባቸው ፡፡
10. አባሪዎች
• አባሪ ሀ ፡- የስትራቴጂካዊ ምንጭ ምድቦች ዝርዝር
• አባሪ ለ ፡- የጨረታ ማስረከቢያ ቅጽ
• አባሪ ሐ ፡- የአቅራቢዎች የሥነ ምግባር ደንብ
አባሪ ሀ ፡- የስትራቴጂካዊ ምንጭ ምድቦች ዝርዝር
አቅራቢዎች ከሚከተሉት ምድቦች ውስጥ አንዱን ወይም ከዚያ በላይ እንዲያመለክቱ ተጋብዘዋል።
1. ቀጥተኛ የኮንስትራከሽን ግብዓቶች
2 የማጠናቀቂያ ግንባታ ግብዓቶች
3. ኤሌክትሮ መካኒካል
4 .ሳኒተሪ ግብኣቶች
5. ኤሌክትሪክና ተዛማጅ ግብኣቶች
6 . ኣለሙኒየምና ብረታ ብረት
7 ቀላልና ከባድ የኮንሰትራክሽን ማሽነሪዎች
8 የግንባታ ባለሙያ ንኡስ ተቋራጮች(እቃ ኣቅረቦት ሳይጨምር)
9 የቴሌኮሚዩኒኬሽን ግብዓቶች
የግብዓቶች ዘርዝር በ16 ገጽ አባሪ ተደርጓል።
አባሪ ለ ፡- የጨረታ ማስረከቢያ ቅጽ
(በጨረታው ተሞልቶ የፕሮፖዛሉ አካል ሆኖ የሚቀርብ)
1. የተጫራቾች መረጃ
• የድርጅቱ ስም ፡- _______________________________
• የምዝገባ ቁጥር ፡- ________________________________
• የግብር ከፋይ ቁጥር፡- __________________________________
• አድራሻ ፡- ______________________________________
• የድርጅቱ ኃላፊ /ተወካይ ስም ፡-- _______________________________
• ኢ-ሜይል፡- ________________________________________________
(ከቢሮ የጸደቀ ኢሜይል ካለ ወይም የተፈቀደለት ሰው ኢሜይል)።
ማሳሰቢያ ፡- ይህ ኢሜይል ለማንኛውም ግንኙነት ስራ ላይ ይውላል ።
2. የተተገበሩ ምድቦች (ከአባሪ ሀ ላይ ምልክት ያድርጉ)
በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመካተት ሃሳባችንን እናቀርባለን እና የአቅራቢዎች የስነምግባር ህግ (አባሪ ሐን) ጨምሮ በፍላጎት መግለጫ (RFP) መስፈርቶችን ላይ የተጠቀሱትን መቀበላችንን እናረጋግጣለን ።
የድርጅቱ ኃላፊ / ተወካይ ፊርማ ፡- _________________________________
ስም እና የስራ ድርሻ ፡- ________________________________
ቀን ፡- _______________________________
የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት ።
አባሪ ሐ ፡ የአቅራቢዎች የሥነ -ምግባር ደንቦች
1. ህጎችን ማክበር : - አቅራቢዎች ሁሉንም የግዥ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ህጎችን ማክበር አለባቸው ፤
2. ታማኝነት :- ከሙስና፣ ማጭበርበር ወይም ሥነ ምግባር የጎደላቸው
3. ጤና እና አካባቢ ደህንነት መጠበቅ :- ደህንነቱ የተጠበቀ የስራ ሁኔታዎችን እና አስፈላጊ የደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎችን መጠቀም፤
4. ምስጥር መጠበቅ - የድርጅቱን ሚስጥር መጠበቅ ፤
5. ቁጥጥር - የአቅራቢዎችን አፈፃፀም ይገመግማል፣ ይከታተላል ፤
6. ከደንብ ውጭ መሆን ፡- - ከአቅራቢው ዝርዝር ውስጥ መወገድ ወይም ኮንትራት መቋረጥ
ያስከትላል ፡፡
ማሳሰቢያ ፡-
እኔ ከዚህ በታች የፈረምኩት ይህንን የአቅራቢዎች የስነ ምግባር ደንብ አንብቤ እና ተረድቼ ለማክበር ተስማምቻለሁ።
የኃላፊ / የተወካይ ፊርማ ፡- ____________________
ስም እና የስራ ድርሻ ፡- ___________________________
የድርጅቱ ስም ፡- _________________________
ቀን፡- ________________________________________________
ለበለጠ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር ፡0912420961
#IPDC
#PMOEthiopia
#ecospecialeconomiczone
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#bolelemiSEZ
#kilintoSEZ
#addisindustryvillage
#informationtechnologypark
#AdamaSEZ
#jimmaSEZ
#HawassaSEZ
#debrebirhanSEZ
#bahirdarSEZ
#kombolchaSEZ
#Arertiindustrypark
#MekeleSEZ
#DDFTZ
#semeraSEZ
#textilehub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#GoldenOpportunity
#TechManufacturing
#fdiready
#StrategicInvestments
#TechManufacturing
#pharmahubafrica
#eastafricasez
#GoldenOpportunity
#itparks
#information
#informationtechnology
#InnovationLeadership
#InnovationInAction
#solarpanels
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30