“ፓርኮቻችን ዉስጥ ያሉ የንግድ ተቋማት ለማህበራዊ ኃላፊነት እያደረጉት ያለውን ሚና አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረግላቸዋል”
አክሊሉ ታደሰ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ
***********************
ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ የንግድ ተቋማት ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዲቀጥሉ ኮርፖሬሽኑ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ገለፁ።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቻይና የንግድ ተቋማት ማህበር በኢትዮጵያ እና የቻይና የገጠር ልማት ፋዉንዴሽን ከቻይና ኤምባሲ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት መርሐ ግብር ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
መድረኩ የቻይና ንግድ ተቋማት በኢትዮጵያ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ረገድ ያበረከቱትን ሁለንተናዊ አስተዋጾ ለማስተዋወቅ ታሳቢ ያደረገ ነዉ፡፡
በፎረሙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አክሊሉ ታደሰ ባደረጉት ንግግር የቻይና መንግስት እና የንግድ ተቋማት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ተሞክሮ ወደ ኢትዮጵያ ለማስፋት እያደረጉት ላሉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው ለአብነትም በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዘመናዊ የህጻናት ማቆያ ገንብቶ ስራ ማስጀመሩን ፤ በተመሳሳይ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክም የአካባቢዉን ወጣቶች በማደራጀት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን የእንሰሳት መኖ ማቀነባበሪያ ስራ ማስጀመሩንና በድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና አካባቢ ላሉ ነዋሪዎች የንጹህ መጠጥ ዉሃ አቅርቦት ስራ እየተሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።
በተጨማሪም ሰራተኞችን በኢኮኖሚ ጫና ተጎጂ እንዳይሆኑ የተለያዩ ምርቶችን የሚያቀርቡ የሰራተኞች ሸማች ማህበራት መደራጀታቸዉን ለአብነት አንስተዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ከሚያደርጋቸዉ የማህበራዊ ኃላፊነት ስራዎች በተጨማሪ የአካባቢ ደህንነትን በማስጠበቅ ረገድ በዘንድሮዉ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና አካባቢያቸዉ 2 ሚሊዮን አገር በቀል እና ለምግብነት የሚዉሉ ችግኞችን ለመትከል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁንና በነገዉ እለትም በሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ በይፋ እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ የቀድሞዉ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ፣ የፋይናንስ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ፣ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር አምባሳደር ዛዎ ዚዮሀን ፤ የብሔራዊ መልሶ ማቋቋሚያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋና ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
"Business institutions in our parks will be given the necessary support to strengthen their role in social responsibility" Aklilu Tadasse IPDC CEO
IPDC CEO l, Aklilu Tadesse, , said that IPDC will provide all necessary support to the business establishments located in the industrial parks managed by the corporation so that the business firms will continue to discharge their social responsibilities effectively.
The CEO said so while addressing an event organized by Chinese Chamber of Commerce in Ethiopia and the Chinese Rural Development Foundation in collaboration with Chinese Embassy in Ethiopia.
The forum is intended to promote the contributions of Chinese business institutions vis-a-vis social responsibilities.
Aklilu Tadesse, thanked Chinese government and business institutions for their efforts to expand their businesses in industrial parks.
The CEO stated that IPDC is paying attention to strengthen its social responsibility. He mention a modern day care facilitu in Bole Limi Industrial Park; animal feed processing plant in Kilinto Industty Park, tap water project in Dire Dawa Free Trade Zone as an example.
He also noted that the corporation work with regards to the establishment of workers' coorporative unions that are providing various merchandizes to workers in order to ease the burden of economic hardship.
In addition to dischargong its social responsibility, IPDC actively engaging in the Green Legacy initiative. As a corportion which promote eco industrial practices, the corporation will plant more than two million seedlings this years in parks the corporation administers, said the CEO.
The corporations this year's Green legacy initiative will be launched today at Semera Industrial Park today.
Dr. Mulatu Teshome, former President of FDRE, Finance Minister, Ahmed Shide, Commissioner of Ethiopian Iinvestment Commission, Lelise Neme, Chinese Ambassador to Ethiopia, Ambassador Zhao Xhyohan,the Commissioner of National Rehabilitation Center, Ambassador Teshome Toga and other senior officials were among the list present to attend the high level event.