• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 5 months ago
  • 572 Views

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በኢትዮጵያ ቻይና ኤምባሲ

በኢንቨስትመንት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከኮርፖሬሽኑ ጋር የጀመርናቸውን ስራዎች አጠናክረን እንቀጥላለን - በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን

በኢትዮጵያ የቻይና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር የሆኑት ዣኦ ዥዩዋን በኢንቨስትመንትና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር የጀመርናቸውን ስራዎች አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ገልፀዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ከሆኑት ዛሆ ዥዮዋን ጋር በኤምባሲያቸዉ ተወያይተዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክሊሉ ታደሰ በውውይቱ ወቅትም በኮርፖሬሽናቸው ስለሚተዳደሩ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ወቅታዊ መረጃዎችን በማቅረብ ቻይናውያን ባለሀብቶች ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የ ነፃ ንግድ ቀጠና ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። መንግስት ለውጪና ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በፖሊሲና በማበረታቻዎች ያደረገውንም ማሻሻያ በዝርዝር አቅርበዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚዉ ቻይናና ኢትዮጵያ በፈተና ዉስጥ ያልዋዠቀ ጠንካራ ወዳጅነትና ትብብር እንዳላቸው አንስተው ይህም ወንድማማችነት ከምንጊዜዉም በበለጠ በኢኮኖሚና በኢንቨስትመንት ዘርፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል።

አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ሀገሪቷ የጀመረችውን የኢንዱስትሪያላይዜሽን ጉዞ እውን ለማድረግ የሚያስችል በቂ ቁመና ላይ መሆኑን ገልፀው ከኮርፖሬሽኑ ጋር ከኢንቨስትመንት ባሻገር በትምህርትና ስልጠና በትብብር ለመስራት ኤምባሲያቸው ሙሉ ዝግጅት እንዳለው አረጋግጠዋል።

በውይይት መድረኩ ከኢንቨስትመንት ፤ ከሰዉ ሀይል ስልጠና ፤ እንዲሁም ከትምህርት እድል በተጨማሪም በሌሎችም የትብብር ማእቀፎች ላይ አብሮ ለመስራት ከስምምነት ተደርሷል።

We will continue to strengthen the work we started with the IPDC in terms of investment and related issues - Chinese Ambassador to Ethiopia Zhao Zhiyuan.

Zhao Zhiyuan, the Chinese ambassador to Ethiopia, said that works will continue to strengthen the started relationship with IPDC regarding investment and related issues.

Aklilu Tadese, IPDC CEO had a fruitful discussion with Zhao Zhiyuan, the Chinese ambassador to Ethiopia.

During the discussion, Mr. Aklilu Tadesse provided updated information about the industrial parks and Dire Dawa Free Trade Zone managed by his corporation and invited Chinese investors to invest in the investment hubs. He also presented in detail the reforms made by the government in terms of policies and incentives for foreign and local investors.

The CEO added that China and Ethiopia have a strong relationship and cooperation that has not wavered in challenges and stated that this brotherhood should be strengthened more than ever in terms of economy and investment. He confirmed that the industrial parks and Dire Dawa Free Trade Zone are convenient places for Chinese investors.

On his part, Ambassador Zhao Zhiyuan that IPDC is in a standard position to realize the industrialization journey that the country has started and confirmed that his embassy is fully prepared to cooperate with IPDC in terms of education and training in addition to investment.