• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 5 months ago
  • 520 Views

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በድሬዳዋ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠናን ጎበኙ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በድሬዳዋ ከተማ የሚገኘውን የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።

በነፃ ንግድ ቀጠናው የሚገኙ የጨርቃጨርቅ አምራች፣ የመኪና መገጣጠሚያና ሌሎች ኩባንያዎችን ተዟዙረው ተመልክተዋል።

የባቡር አገልግሎት በአዲስ እና በዘመነ ሁኔታ ተገንብቶ ስራ መጀመሩ እና ከተማዋ ከወደብ በቅርበት ርቀት ላይ መገኘቷ ለነፃ ንግድ ቀጠናው ውጤታማነት ብሎም ድሬዳዋን ለቢዝነስ ተቋማት ተመራጭ ቦታ እንደሚያደርጋት በወቅቱ ተጠቁሟል፡፡

በጉብኝቱ የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና አመራሮች እንዲሁም የከተማዋ የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና በአሁን ሰዓት ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍሰት እያስተናገደ ያለ ነፃ ንግድ ቀጠና ሲሆን በኢትዮጵያ በዘርፉም የመጀመሪያ እንደሆነ ይታወቃል።

Deputy Prime Minister and Minister of Foreign Affairs Mr. Demeke Mekonon visited Dire Dawa Free Trade Zone

Deputy Prime Minister and Minister of Foreign Affairs Demeke Mekonon observed the current activities of Dire Dawa Free Trade Zone in Dire Dawa.

He visited textile manufacturers, auto assembly and other companies in the free trade zone.

It was pointed out at the time that the new and up-to-date railway service and the fact that the city is close to the port will make the free trade zone an ideal location for business establishments.

The management of Dire Dawa Free Trade Zone as well as various officials of the city were present during the visit.

Dire Dawa Free Trade Zone is a free trade zone that is hosting a large flow of investment and is known to be the first in the sector in Ethiopia.