• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 4 months ago
  • 353 Views

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን "ጎልደን ሪሴፕሽን"

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ "ጎልደን ሪሴፕሽን" አገልግሎት በይፋ አስጀመረ

ዛሬ የተጀመረውና ጎልደን ሪሴፕሽን ተብሎ የተጠራው የኮርፖሬሽኑ አዲስ አገልግሎትበማምረት በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት በማድረግ፣ በስራ እድል ፈጠራ፣ በኤክስፖርት ምርት፣ ተኪ ምርት እና በሌሎችም የማክሮ ኢኮኖሚ አመላካቾች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስተሮች ቢዝነሳቸውን ለመከታተልና ለመመልከት ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡበት ወቅት ከአየር መንገድ ጀምሮ የሚደረግላቸው የ VIP አቀባበል ስነ-ስርዓት እንደሆነ ተገልጿል።

በዛሬው እለት የተጀመረው ይህ ፕሮግራም ኢንቨስተሮች በሚመጡበት ወቅት ከኮርፖሬሽኑ የበላይ ኃላፊዎች በተጨማሪ በየወቅቱ ኢንቨስተሮቹ ካላቸው ቢዝነስ ጋር ተያያዥ የሆኑ አገልግሎት ሰጪ የመንግስት ተቋማት ኃላፊዎች ጭምር አቀባበል እንዲያደርጉ በማሰብ የተዘጋጀ አገልግሎት መሆኑም ተጠቅሷል።

በዚሁ መሰረት ኢንቨስተሮቹ ወደ ሀገር ሲገቡ ልዩ መግቢያ (VIP) እንዲመቻችላቸው፣ ከአየር መንገድ እስከ ሆቴልና ማረፊያቸው ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት በተቋሙ ሀላፊ አሸከርካሪነት እንዲሰጣቸው፣ የተቋሙ የበላይ ሀላፊዎችም የክብር እጅባ እንዲያደርጉላቸው የሚያደርግ ሲሆን በቆይታቸው ሁሉ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ፣ እንደገቡ የሆቴል መስተንግዶ እንዲያገኙና የሀገራችንን ባህላዊ የቡና ስነ-ስርዓት እንዲጋበዙ የሚያስችል አገልግሎት ነው።

በዚሁ አግባብ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ካፒታል በማስመዝገብ ቀደምት የሆነውና በስራ እድል ፈጠራ፣ በኤክስፖርት እና በመሰል የማክሮ ኢኮኖሚ አመላካቾች ከፍተኛ ውጤት በማስመስገብ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በምርት ሂደት ላይ የሚገኘው የሺንትስ ኩባንያ ፕሬዝዳንት እና ባለቤት ቻ ሚን ሆ ከትዳር አጋራቸው ኬዩም ሺክ ጋር ኢትዮጵያ ሲገቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ሺንትስ የጨርቃጨርቅና ጋርመንት ኩባንያ መሰረቱን ደቡብ ኮርያ ያደረገ ሲሆን እ.አ.አ በ2014 በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ የጀመረና ከ5 ሺ በላይ ሰራተኞችን ቀጥሮ እያሰራ ያለ አለም አቀፍ የጨርቃ ጨርቅና ጋርመንት አምራች ነው።

IPDC officially launched the "Golden Reception" service 

The new service of IPDC, which was launched today and called 'Golden Reception', is a new service for foreign direct investors who have achieved high results in macroeconomic indicators by investing in various sectors in industrial parks and Dire Dawa Free Trade Zone, in job creation, export, import substitution, and other macroeconomic indicators. It is said that it is a VIP welcome ceremony for them starting from the Airport.

It was also mentioned that this program, which started today, is designed to welcome the investors, by IPDC top Management also officials of other government institutions that provide services related to the business of the investors.

Accordingly, when the investors enter the country, they will get a service of special entrance (VIP), transportation from the airline to their hotel by the head of IPDC, hand of honor by top officials of institutions , and they will get transportation services throughout their stay, receive hotel hospitality upon arrival, and enjoy the traditional coffee ceremony of our country.

CHA MIN HO, the president and owner of Shints Company, which is the first to record high investment capital and has achieved high results in terms of job creation, export and similar macroeconomic indicators, which is in operation at Bole Lemi Industrial Park, was welcomed when he entered Ethiopia with his life partner Madam SHIN KEUM SHIK.

Shintz Textile and Garment Company is an international textile and garment manufacturer based in South Korea that started operation in 2014 at Bole Limi Industrial Park and employs more than 5,000 workers.