• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 6 months ago
  • 584 Views

የኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነት የፖሊሲ እና የስትራቴጂ ትግበራ ረቂቅ ሰነድ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች የኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነት የፖሊሲ እና የስትራቴጂ ትግበራ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄደ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና በዋተር ዊትነስ ኢንተርናሽናል ትብብር የተዘጋጀና ኮርፖሬሽኑ እንደ ሀገር ያለበትን ማህበራዊ ኃላፊነት በዘላቂነት መወጣት እንዲችል የሚያግዝ የፖሊሲ እና ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ሰለሞንን ጨምሮ ሌሎች የኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎች፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ስራ አስኪያጆች እንዲሁም ዋተር ዊትነስ እና ጥናቱን ያዘጋጁ የስትራቴጂ እና የፖሊሲ አማካሪዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ኮርፖሬሽኑ እንደ ሀገር በተለያዩ ግዜያት ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለረጅም ግዜ እየተወጣ መቆየቱን አንስተው አሁን ላይ ሁሉንም መሰልና ተያያዥ ስራዎች በፖሊሲና በስትራቴጂ መደገፍ ጊዜው የሚጠይቀው እና መሰረታዊ መሆኑን በማሳወቅ መድረኩን በይፋ አስጀምረዋል።

በመድረኩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እንዲሁም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ አምራች ኩባንያዎች የማህበራዊ ኃላፊነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ለምን እንደሚያስፈልጋቸው፣ እንዴት ተፈፃሚ እንደሚሆን፣ አላማው እና ተግባራዊነቱ በሰነዱ በዝርዝር ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።

የፖሊሲና ስትራቴጂ ሰነዱ ቦሌ ለሚ፣ ሀዋሳ እና አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን መነሻ አድርጎ የተዘጋጀ ሲሆን ኮርፖሬሽኑ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከሚሰሩ አምራች ኩባንያዎች እና አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ በአለም አቀፍ ስታንዳርድ መሰረት ወጥ በሆነ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ እንዲመራ የሚያግዝ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።

A discussion was held on the draft document of Corporate Social Responsibly ( CSR ) implementation strategy for IPDC and Industrial Parks

The discussion was held on the draft policy and strategy document prepared by the collaboration of IPDC and Water Witness International, which will help the corporation fulfill its social responsibility as a country in a sustainable manner.

In the discussion, IPDC Deputy CEO, Mr. Shiferaw Solomon, other offials of the Corporation, managers of Industrial Parks and Water Witness also Strategy and policy advisors who organized the documents were participated.

IPDC Deputy CEO, Mr. Shiferaw Solomon, who made the opening remarks at the forum, pointed out that IPDC as a corporation and as a country has been fulfilling its social responsibility for a long time and announced that supporting all similar and related activities with policy and strategy is timely and is fundamental.

In the forum, points regarding why IPDC and manufacturing companies located in industrial parks need a social responsibility policy and strategy, how it will be implemented, its purpose and practicality were presented in detail in the document and discussion was held.

The policy and strategy document was prepared based on Bole Lemi, Hawassa and Adama Industrial Parks, and it was stated in the forum that it helps IPDC to be guided by a uniform policy and strategy in accordance with international standards when it fulfills its social responsibility in cooperation with the manufacturing companies and partner institutions working in the industrial parks.