• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 7 months ago
  • 540 Views

የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች ውይይት

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች "የፀጥታ መዋቅር ሪፎርምና የክልል ልዩ ኃይሎችን መልሶ ማደራጀት" ላይ በተዘጋጀ ሰነድ ዙሪያ ተወያይተዋል።

የውይይት መድረኩን የመሩት የኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ሰለሞን በውይይቱ የሀገር አንድነትን ለማረጋገጥና የህዝቦችን አብሮነት ለማስቀጠል የፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ሪፎርም ማድረግ አስፈላጊነት ላይ ሁሉም ዜጋ የጋራ ግንዛቤ ፈጥሮ ለተግባራዊነቱ ሊተባበር ይገባል ብለዋል።

አቶ ሽፈራው በተጨማሪም የሀገር አንድነት የሚጠበቀውና የህዝቦች ሰላም የሚረጋገጠው በአንድ ማዕከል በሚመራ የፀጥታ መዋቅር እንጂ በተበታተነ ኃይል ባለመሆኑ ሀገራዊ የሆነ የፀጥታ መዋቅር እንዲኖረን ሁሉም ዜጋ የራሱን ድርሻ መወጣት እንደሚኖርበት አፅንኦት ሰጥተዋል።

ለመድረኩ የመወያያ ሰነዱን በዝርዝር ያቀረቡት የማርኬቲንግና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘመን ጁነዲ በበኩላቸው ባለፉት 4 አመታት ተቋማቶቻችን ሁሉንም ዜጋ በእኩል የሚያዩና የሚያገለግሉ እንዲሆኑ ለማድረግ የሪፎርም ስራዎች መሰራታቸው አስፈላጊ መሆኑንና ለዚህም ሁሉም ዜጋ ጠንካራ የፀጥታና የደህንነት ብሎም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት እንዲኖሩን የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይኖርበታል ብለዋል።

አቶ ዘመን አያይዘውም የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊትን መንግስት ይበልጥ እያጠናከረ ያለበት መንገድ አገሪቱ በቀጠናው በተለይም በቀይ ባህር ቀጠና አካባቢ እየታየ ላለው የሀይል ሽሚያ የሚመጥን እንደሆነና እጅግ ዘመናዊና ጠንካራ ሰራዊት መገንባቱ ከአገሪቱ አልፎ ለአህጉሩ መመኪያ የሆነ ህዝባዊ ሰራዊትን እንዲኖር የሚያስችል ነዉ ብለዋል ።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የመወያያ ሰነዱ መቅረቡና በአስፈላጊነቱ ላይ የጋራ ውይይት መደረጉ በሀገር አንድነት ላይ ሁሉም በጋራ እንዲሰራ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀው በወቅቱ ሰነዱ ወደ ታች ወርዶ ለውይይት አለመቅረቡና የጋራ መግባባት ተፈጥሮ ወደ ስራ አለመገባቱ እንደክፍተት የሚታይ መሆኑን ጠቁመዋል።