የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሚሳተፍበት የኢትዮ-ፓኪስታን የንግድ ፎረም መካሄድ ጀመረ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና ሌሎች የፌደራል ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች የሚሳተፉበት የኢትዮ-ፓኪስታን የንግድ ፎረም በይፋ ተጀምሯል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ40 ዓመታት በኋላ ወደ ፓኪስታን ቀጥታ በረራ በድጋሚ የጀመረበትና በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚመረቅበት። ፎረሙን ለየት ያደርገዋል ተብሏል።
በፎረሙ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በፓኪስታን የሚገኙ የቢዝነስ ተቋማትና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ኢንቨስት እንዲያደርጉ በዝርዝር የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ የሚገኙ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢንቨስትመንት ስምምነቶች እና የመግባቢያ ሰነዶች ተፈርመው የፓኪስታን እና የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ፣ የኢንቨስትመንትና የፖለቲካ ትስስር ይጠናከራል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህ ቀደም የፓኪስታን ባለሀብቶች የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሚያስተዳድራቸውን ኢንዱስትሪ ፓርኮች የጊበኙ ሲሆን ፎረሙም የጉብኝቱ ቀጣይ አካል እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
በፎረሙ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ንግድ ሚኒስቴር፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ቻምበር ኦፍ ኮሜርስ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
Ethio-Pakistan business forum, in which IPDC is participating, is being held in Pakistan
The Business Forum has been officially launched in the presence of IPDC CEO, Aklilu Tadesse and other federal senior officials of different institutions.
It is said that the forum is different from other forums because Ethiopian Airlines has restarted direct flights to Pakistan after 40 years and the Ethiopian Embassy in Pakistan will be inaugurated.
At the forum, the CEO of the corporation Aklilu Tadesse is discussing detailed investment issues with business institutions and investors in Pakistan to invest in Ethiopian industrial parks, and along with this, investment agreements and memorandums of understanding will be signed. It is expected that the economic, investment and political ties between Pakistan and Ethiopia will be strengthened.
Earlier, Pakistani investors visited the industrial parks managed by IPDC and this forum is the next part of the visit.
Ministry of Foreign Affairs, Ministry of Trade, Industrial Parks Development Corporation, Investment Commission and Ethiopian Chamber of Commerce are participating in the forum.